ለተቃውሞ የወጡ የካሜሮን ምሁራን በፖሊስ ተደበደቡ

የካሜሮን ምሁራን
ታትሟል

ሶስት የካሜሮን ምሁራን በመዲናዋ ያውንዴ ከስራ ጋር በተያያዘ ተቃውሞ መውጣታቸውን ተከትሎ በፖሊስ ተደብድበዋል።

ተጎድተውም ለህክምና ወደ ሆስፒታል ስለመወሰዳቸውም ተዘግቧል።

ሌላ የአርባ አምስት አመት እድሜ ያላት ተቃዋሚ ደግሞ መርዝ በመውሰዷ በፍጥነት ወደ ሆስፒታል ተወስዳለች ተብሏል።

ከሁለት መቶ በላይ የሚሆኑ ፒኤችዲ ያላቸው የያዘው ይህ የምሁራን ቡድን አባላት የመንግሥት ዩኒቨርስቲዎች አውቀው ያገሉናል በማለት ተቃውሟቸውን አንስተዋል።

ምሁራኖቹ በመንግሥት ዩኒቨርስቲዎችም ለአመታት በፈቃደኝነት በማገልገል ላይ ናቸው ተብሏል።

የቡድኑ ቃል አቀባይ ናናን ሄርማን እንዳሉት በዩኒቨርስቲዎች ብዙ ጊዜ የሚቀጠሩት ከነሱ ያነሰ የትምህርት ብቃት ያላቸው ናቸው ብለዋል።

የከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ጃኩዌስ ፋሜ እንዶንጎ ከሰሞኑ ምሁራኑ ያላቸውን ቅሬታዎች እንደሚያዩ ቃል በመግባት፤ እስካሁንም ያለው ቅጥር በብቃት ነው የሚለውን አስምረውበታል።

አንዳንድ ተቃዋሚዎች በሚኒስቴሩ ዋና ቢሮ የረሃብ አድማ ያነሱ ሲሆን መንግሥት እስኪቀጥራቸውም ድረስ በአድማው እንደሚቀጥሉበት አስጠንቅቀዋል።