ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
በዲሞክራቲክ ኮንጎ 16 ተሳፋሪዎች የጫነ አውሮፕላን መኖሪያ ቤቶች ላይ ተከሰከሰ
ታትሟል
አስራ ስድስት ተሳፋሪዎችን እና ሁለት የአውሮፕላን ሰራተኞችን አሳፍሮ የነበረው አውሮፕላን ጎማ ከተማ መኖሪያ ቤቶች ላይ መከስከሱን የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ሰሜናዊ ክልል ኪቩ ገዥ ናዛናዙ ካሲቪታ አስታውቀዋል።
በመነሳት ላይ ሳለ ችግር የገጠመው ይህ አውሮፕላን በአንድ ደቂቃ ውስጥ የተከሰከሰው በጎማ ከተማ ማፔንዶ በተሰኘ ሰፈር መኖሪያ ቤቶች ላይ ነው።
በአውሮፕላኑ አደጋ ሰዎች መሞታቸውን የተናገሩት ገዥው ምን ያህል ሰዎች ለሚለው ግን ቁጥር አላስቀመጡም።
አውሮፕላኑ ቢዚ ቢ የተባለ የግል አየር መንገድ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።
አውሮፕላኑ ከጎማ ከተማ የተነሳው ወደ ቤኒን ለማቅናት ነበር።
የአቪዬሽን ደህንነት ቁጥጥር የላላ ነው በሚባልባት በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የአውሮፕላን አደጋ ይደጋገማል። አውሮፕላን ጥገና ችግርም ለተደጋጋሚ አደጋዎች በምክንያትነት ይቀመጣል።
የአገሪቱ ሁሉም የግል አየር መንገዶች በአውሮፓ እንዳይንቀሳቀሱ በአውሮፓ ህብረት ዕግድ ተጥሎባቸዋል።