የ2011 ዓ.ም አበይት ክንውኖች በፎቶ

ታትሟል

ዛሬ 2011 ዓ. ም. ን ተሰናብተን 2012 ዓ. ም ን ተቀብለናል። ያለፈውን ዓመት ወደኋላ ስንቃኘው አበይት ከነበሩት ክንውኖች ጥቂቱን መራርጠን እንዲህ በምስል አጠናቅረነዋል።

ይናገራል ፎቶ. . . ይባል የለ?

የሲዳማ የክልልነት ጥያቄ በዓመቱ ጎልተው ከወጡ ኩነቶች አንዱ ነው

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, የሲዳማ የክልልነት ጥያቄ በዓመቱ ጎልተው ከወጡ ኩነቶች አንዱ ነው
ሱዳን ባለፈው ዓመት ከፍተኛ ቀውስ ውስጥ መክረሟን ተከትሎ ውጥረቱን ለማርገብ ኢትዮጵያ ጥረት እያደረገች እንደነበር ይታወሳል

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, ሱዳን ባለፈው ዓመት ከፍተኛ ቀውስ ውስጥ መክረሟን ተከትሎ ውጥረቱን ለማርገብ ኢትዮጵያ ጥረት እያደረገች እንደነበር ይታወሳል
የጤና ጥበቃ ሚንስትር በየወሩ ከመኪና ነጻ ቀን የጀመረው በ2011 ዓ. ም. ነበር

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, የጤና ጥበቃ ሚንስትር በየወሩ ከመኪና ነጻ ቀን የጀመረው በ2011 ዓ. ም. ነበር
በአፋር 3.8 ሚሊዮን ዓመት ያስቆጠረ ሙሉ የራስ ቅል መገኘቱ የተገለጸበት ዓመትም ነበር

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, በአፋር 3.8 ሚሊዮን ዓመት ያስቆጠረ ሙሉ የራስ ቅል መገኘቱ የተገለጸበት ዓመትም ነበር
አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ ወደ ኢትዮጵያ ሲመጣ ጠቅላይ ሚንስትሩ አቀባበል አድርገውለታል

የፎቶው ባለመብት, OFFICE OF THE PRIME MINISTER

የምስሉ መግለጫ, አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ ወደ ኢትዮጵያ ሲመጣ ጠቅላይ ሚንስትሩ አቀባበል አድርገውለታል
ዘንድሮ 350 ሚሊዮን ችግኞች በመላው አገሪቱ መተከሉ ተገልጿል

የፎቶው ባለመብት, MICHAEL TEWELDE

የምስሉ መግለጫ, ዘንድሮ 350 ሚሊዮን ችግኞች በመላው አገሪቱ መተከሉ ተገልጿል
የ2011 የኢትዮጵያን ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ ያነሳው መቀለ 70 እንደርታ

የፎቶው ባለመብት, MICHAEL TEWELDE

የምስሉ መግለጫ, የ2011 የኢትዮጵያን ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ ያነሳው መቀለ 70 እንደርታ
ጠቅላይ ሚንስትሩ ከካቢኔያቸው 50 በመቶውን ሴቶች አድርገዋል

የፎቶው ባለመብት, GEGNIT ETHIOPIA/ TWITTER

የምስሉ መግለጫ, ጠቅላይ ሚንስትሩ ከካቢኔያቸው 50 በመቶውን ሴቶች አድርገዋል
በኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን የበረራ ቁጥር ኢቲ 302 የተሳፈሩ 157 ተጓዦች ሕይወታቸውን አጥተዋል

የፎቶው ባለመብት, Jemal Countess

የምስሉ መግለጫ, በኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን የበረራ ቁጥር ኢቲ 302 የተሳፈሩ 157 ተጓዦች ሕይወታቸውን አጥተዋል
የዛላምበሳ ድንበር የዛሬ ዓመት ለእንቁጣጣሽ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድና ኢሳያስ አፈወርቂ በተገኙበት ተከፍቶ ነበር። ነገር ግን ብዙም ሳይቆይ ከወራት በኋላ ባልታወቀ ምክንያት ተዘግቷል።

የፎቶው ባለመብት, Yonas Fisehaye

የምስሉ መግለጫ, የዛላምበሳ ድንበር የዛሬ ዓመት ለእንቁጣጣሽ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድና ኢሳያስ አፈወርቂ በተገኙበት ተከፍቶ ነበር። ነገር ግን ብዙም ሳይቆይ ከወራት በኋላ ባልታወቀ ምክንያት ተዘግቷል።
የቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንቶች ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳና ግርማ ወ/ጊዮርጊስ በዚህ ዓመት ነበር ይህቺን ዓለም በሞት የተሰናበቱት
የምስሉ መግለጫ, የቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንቶች ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳና አቶ ግርማ ወ/ጊዮርጊስ በዚህ ዓመት ነበር ይህቺን ዓለም በሞት የተሰናበቱት