አባትና ልጅ ከ58 ዓመታት በኋላ በፌስቡክ አማካኝነት ተገናኙ
ታትሟል
ጁሊ ሉንድ ከ58 ዓመታት በኋላ አባቷን አግኝታለች። ጁሊ አብዛኛውን ዕድሜዋን ያሳለፈችው አባቷን በመፈለግ ነው።
የሚገርመው ግን አባቷ በሚኖርበትና እርሷ በምትኖርበት ከተማ መካከል ያለው ርቀት የአንድ ሰዓት የመኪና ጉዞ ብቻ ነው።
የሚገናኙበት እድል ባለመፈጠሩ ግን ለ58 ዓመታት ተለያይተዋል።
በቅርቡ እናቷንና የእንጀራ አባቷን ያጣችው ጁሊ አባቷን ለማግኘት አንድ አማራጭ ዘየደች። አባቷን በፌስቡክ አማካኝነት መፈለግ።
ጥረቷ መና አልቀረም። ተሳክቶላት ከ58 ዓመት በኋላ ከአባቷ ጋር ተገናኝተዋል።