“ከደረሰብኝ ጥቃት አንፃር ልጄን ሌላ ሰው ወስዶት ስለእናቱ ታሪክ ሳያውቅ እንዲያድግ እመኛለሁ"

የተንቀሳቃሹ ምስል መግለጫ, “ከደረሰብኝ ጥቃት አንፃር ልጄን ሌላ ሰው ወስዶት ስለእናቱ ታሪክ ሳያውቅ እንዲያድግ እመኛለሁ"
ታትሟል

ዘሃራ አብዱ [ስሟ ተቀይሯል] የህወሓት ወታደሮች ወደምትኖርበት ከተማ ሲገቡ ከባለቤቷ ጋር ወደ ገጠር ሸሽተዋል::

የገጠሩ ኑሮ ግን ከአንድ ወር በላይ የሚገፋ አልሆነም። የህወሓት ወታደሮች አካባቢውን ባይለቁም አካባቢው የተረጋጋ ሲመስላቸው ወደ መኖሪያ ከተማቸው መመለስን መረጡ።

መስከረም 16/2014 ዓ.ም ወደሚኖሩባት ከተማ እያመሩ መንገድ ላይ በህወሓት ወታደሮች ተያዙ። ወታደሮቹ ዘሃራን ለመድፈር ሞከሩ። ባለቤቷ 'ሚስቴ ስትደፈር አላይም' በሚል ሁለቱን ወታደሮች ገድሎ ራሱን አጠፋ። በዘሃራ ላይም መደፈርን ጨምሮ ብዙ ጾታን መሠረት ያደረጉ በደሎች እንደተፈፀሙባት ትናገራለች።

ዘሃራ ይህንን እና ሌሎች ታሪኮቿን ከቢቢሲ ጋር በነበራት ቆይታ አጋርታናለች።