ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
ታዋቂው ተዋናይ ዦን ክላውድ ቫን ዳም የኮንጎ ዲፕሎማቲክ ፓስፖርት ተሰጠው
ታዋቂው ቤልጂየማዊ የሆሊዉድ የፊልም ተዋናይ ዦን ክላውድ ቫን ዳም የኮንጎ ዲፕሎማቲክ ፓስፖርት ማግኘቱ እንዳስደሰተውና ሌሎች ተዋናዮችም ዴሞክራቲክ ኮንጎን እንዲጎበኙ እንደሚያደርግ አስታውቋል።
‘’እንደ ሲልቬስተር ስታሎን፣ ሽዋዝኒገር እና ጃኪ ቻን ያሉ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቁ ተዋናዮች ኮንጎን እንዲጎበኙቨለማሳመን እሞክራለው’’ ብሏል የ61 ዓመቱ ቫን ዳም በዋና ከተማዋ ኪንሻሳ ፓስፖርቱን ሲቀበል።
ቫን ዳም የአገሪቱ የባህል፣ የወጣቶችና የዱር እንስሳት አምባሳደር ተደርጎም ተመርጧል።
‘’ሌሎችም ታዋቂ ሰዎች መምጣት ይችላሉ። ታዋቂዋ ዘፋኝ ጄኒፈር ሎፔዝ፣ ክርስቲያኖ ሮናልዶ፣ ሊዮኔል ሜሲን የመሳሰሉ ሰዎች ወደ ኮንጎ በመምጣት አገሪቱ ሰላማዊ መሆኗን ማሳየት አለባቸው። ኮንጎ ለታዋቂ ሰዎች ምቹ መሆኗን እና ደህንነታቸውን መጠበቅ እንደምትችል ማስገንዘብ አለባቸው።’’
ዴሞክራቲክ ኮንጎ ለአስርታት ሰላምና መረጋጋት ርቋት የቆየች አገር ስትሆን በምስራቃዊ ክፍል የሚገኘው በማዕድን የበለጸገ አካባቢ ደግሞ በበርካታ የታጠቁ ቡድኖች መካከል ለሚከሰቱ ግጭቶች ምክንያት ነው። ግድያያ፣ ዝርፊያ እንዲሁም አስገድዶ መድፈር ወንጀሎች በአካባቢው በተደጋጋሚ እንደሚከሰቱ በተለያዩ ጊዜያት ይዘገባል።
በአንድ ወቅት የማርሻል አርትስ አሸናፊ የነበረው ቫን ዳም እንደ ሳይቦርግ፣ ኪክቦክሰር፣ ዩኒቨርሳል ሶልጀር እንዲሁም ዘኩዌስት በተሰኙ ፊልሞቹ ዓለም አቀፍ እውቅናን ማትረፍ የቻለ ተዋናይ ነው።
ተዋናዩ ፓስፖርቱን ካገኘ በኋላ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ዶሜክራቲክ ኮንጎ ውስጥ መወለዱን በመግለጽ በርካቶችን አስገርሟል። ቫን ዳም በዴሞክራቲክ ኮንጎ ደቡብ ምስራቃዊ ክፍል በመትገኘው ሊካሲ ከተማ እንደተወለደም ተናግሯል።
ይህ ደግሞ ዴሞክራቲክ ኮንጎ ከቤልጂየም ቁጥጥር ነጻነቷን ያወጀችበት ዓመት ነው። ቫን ዳም አክሎም ወደ ኮንጎኢንቨስትመንት መሳብ ከፍተኛ ጥቅም እንደሚኖረው አስረድቷል።
‘’በዴሞክራቲክ ኮንጎ ያለው ማዕድን ቢተመን እስከ 36 ትሪሊየን ዶላሮችን ያወጣል። የእኔ ኃላፊነት የሚሆነው አገሪቱውስጥ ገንዘባቸውን ማፍሰስ የሚፈልጉ ሰዎችን ማግኘትና መጀመሪያ ግን ለዜጎች በጎ ነገር ማበርከት እንዳለባቸውማሳሰብ ነው። በተጨማሪም ከፕሬዝዳንት ፌሊክስ ሺኬዱ ጋር በትልቅ መተማማን መስራት እንደሚችሉ ማሳየትእፈልጋለው’’ ብሏለ በጋዜጣዊ መግለጫው ወቅት።
ነገር ግን በዴሞክራቲክ ኮንጎ ሕገ መንግስት ላይየሁለት አገር ዜጋ መሆን የተከለከለ ሲሆን አንዳንዶችም የቫን ዳምአዲሱ ፓስፖርት ምን ያክል ውጤታማና ጠቃሚ ይሆናል የሚለው ላይ ስጋታቸውን ገልጸዋል።