ኮምቦልቻ፡ በጦርነቱ ሐብታቸውንም ጤናቸውንም ያጡት እናት
ታትሟል
ወይዘሮ አስቴር የህወሓት ወታደሮች ኮምቦልቻን በተቆጣጠሩ ማግስት ነው ጥቃት የተፈጸመባቸው። በተዘጋው የመኖሪያ ቤታቸው በር በኩል የተተኮሱ ሦስት ጥይቶች ወይዘሮ አስቴር ላይ አርፈዋል። የሕክምና አገልግሎቶች ተዘጋግተው በነበሩበት በዚያ አስቸጋሪ ወቅት ጉዳት ያስተናገዱት ወይዘሮ አስቴር፣ አሁን ከእዚያ አሰቃቂ ጥቃት ተርፈው ታሪካቸውን አውርተውናል።