ዓለም ችላ ያለው በወር 700 የአየር ጥቃቶች የተፈጸመበት የየመኑ ጦርነት

የተንቀሳቃሹ ምስል መግለጫ, ዓለም ችላ ያለው በወር 700 የአየር ጥቃቶች የተፈጸምበት የየመኑ ጦርነት
ታትሟል

ስምንት ዓመታትን ያስቆጠረው የየመኑ ጦርነት ከባድ ሰብአዊ እና ቁሳዊ ጥፋትን ቢያስከትልም ተገቢውን የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብን ትኩረት አላገኘም።

በሳዑዲ አረቢያ እና በዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ የሚመራው ጥምር ኃይል በኢራን በሚደገፉት ሁቲ አማጺያን ላይ በሚያካሂዱት ደተጋጋሚ የአየር ጥቃቶች በርካታ ሰላማዊ ሰዎች ህይወታቸውን እያጡ ነው።

በቅርቡ በአንድ ወር ብቻ ሰባት መቶ የአየር ጥቃቶች መፈጸማቸው የተነገረ ሲሆን፣ በዚህ ችላ በተባለው የየመን ጦርነት በአየር ጥቃቶች የሚደርሱ ጉዳቶችን አሳሳቢ ሆነዋል።