የሩሲያ እና የዩክሬን ጦርነት የአንድ ሳምንት ዋና ዋና ክሰተቶች

የተንቀሳቃሹ ምስል መግለጫ, የሩሲያ እና የክሬን ጦርነት የአንድ ሳምነት ዋና ዋና ክሰተቶች
ታትሟል

ሩሲያ በጎረቤቷ ዩክሬን ላይ ጥቃት ልትከፍት እየተዘጋጀች እንደሆነ ምዕራባውያን ለወራት ሲወተውቱ ቆይተዋል። ሩሲያም ከዚህ ድርጊት እንድትቆጠብ ሲመክሩም ሲያስጠነቅቁም ቆይተዋል።

ሩሲያም የኔቶ መስፋፋት በዩክሬን በኩል ቀስ በቀስ ወደ ድንበሯ እየተጠጋ መምጣቱ ለደኅንነቷ ስጋት መሆኑን በመግለጽ እየተዘጋጀች መሆኑንና አስፈላጊውን እርምጃ እንደምትወስድ ስትገልጽ ነበር።

በመጨረሻም የተፈራው እውን ሆነ ሩሲያ ከአንድ ሳምንት በፊት ጦሯን በክሬን ላይ አዝምታ ወረራ ከፈተች። ዓለምም በእጅጉ ተደናግጦ ማዕቀብ፣ መግለጫና ውግዘትን በሩሲያ ላይ በተከታታይ አሳላፈ። ጦርነቱ ግን አሁንም እንደቀጠለ ነው።

ባለፈው አንድ ሳምንት ውስጥ የታዩትን ዋና ዋና ክሰተቶች ከቪዲዮው ይመልከቱ።