በተውሶ ስልክ በሰሩት ፊልም ኔትፍሊክስ ላይ ተወዳጅ ለመሆን የበቁት ወጣቶች

የተንቀሳቃሹ ምስል መግለጫ, በተውሶ ስልክ በሰሩት ፊልም ኔትፍሊክስን የተቆጣጠሩት ናይጄሪያውያን
ታትሟል

ካዱና በተባለች የናይጄሪያ ከተማ ዘጠኝ ወጣቶች ሳይንሳዊ ልቦለድ ፊልም መሥራት ጀመሩ።

ትራይፖድ ከእንጨት በመስራት እና ከቤተሰብ ለቀረጻ የሚሆን ዘመናዊ ስልክ በመዋስ ነበር በ2016 [እአአ] ሥራቸውን የጀመሩት።

ከሦስት ዓመታት በኋላ አንደኛው አጭር ቪዲዮ የሆሊውድ የፊልም ኮከቦችን ሳይቀር ቀልብ መሳብ ቻለ። አሁን ፊልማቸው ኔትፍሊክስ ላይ በመታየት ነው።