ከቀሪው ዓለም ለየት የሚለው የቻይናውያን አዲስ ዓመት እና አከባበሩ

የተንቀሳቃሹ ምስል መግለጫ, የቻይና አዲስ ዓመት በምንድን ነው የሚለየው?
ታትሟል

ቻይናውያን አዲስ ዓመታቸውን ሰኞ ጥር 24/2014 ዓ.ም ይይዛሉ። በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ቻይናውያን የአዲስ ዓመት ክብረ በዓልን ከቤተሰቦቻቸው ጋር ለማክበር ከተለያዩ ስፍራዎች ወደ ቤተሰቦቻቸው ያቀናሉ።

የቻይናውያን የዘመን አቆጣጠር ከቀሪው ዓለም ለየት ያለ ሲሆን እያንዳንዱ ዓመት በተለያዩ እንስሳት ይወከላል። የአሁኑ አዲስ ዓመትም በነብር ተሰይሟል።

የቻይናውያንን የዘመን አቆጣጠርና የአዲስ ዓመት አከባበር በተመለከተ ዋና ዋና ጉዳዮችን የሚዳስሰውን ይህንን ቪዲዮ ይመልከቱ።