አሰቃቂው የኢትዮጵያውያን ሁኔታ በሳዑዲ አረቢያ እስር ቤቶች
ታትሟል
በተለያዩ የሳዑዲ አረቢያ እስር ቤቶች የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ እንግልት እንደሚደርስባቸው በመግለጽ መንግሥት ወደ አገር ቤት እንዲመልሳቸው ጥሪ ሲያቀርቡ በተደጋጋሚ ይደመጣሉ።
ቢቢሲ ኢትዮጵያውያኑ እስረኞች ያሉበትን ሁኔታ የሚያሳይ ቪዲዮ የደረሰው ሲሆን በዚህ ተንቀሳቃሽ ምስል ላይም ልብሳቸው አልቆ፣ ጥቁር ፌስታል ለብሰው እና ተጎሳቁለው ይታያሉ።

በርካታ ኢትዮጵያውያን በነዳጅ ሃብት ወደ በለጸገችው ሳዑዲ አረቢያ በመጓዝ በተለያዩ የሙያ መስኮች ይሰማራሉ።
ኢትዮጵያውያኑ ላለፉት በርካታ ወራት የሚናገሩት ግን ሠርቶ ስለመቀየር ሳይሆን ስለሚደርስባቸው መከራ እና ግፍ ሆኗል።