በባቡር ሐዲድ ላይ የወደቀው አውሮፕላን ፓይለት በባቡር ከመገጨት ተረፈ

የተንቀሳቃሹ ምስል መግለጫ, በባቡር ሐዲድ ላይ የወደቀው አውሮፕላን ፓይለት በባቡር ከመገጨት ተረፈ
ታትሟል

አሜሪካ ሎስ አንጀለስ ውስጥ ከአንድ አውሮፕላን ማረፊያ አቅራቢያ ካለ የባቡር ሐዲድ ላይ በድንገት የተከሰከሰው አነስተኛ አውሮፕላን አብራሪ ሌላ አደጋ ገጥሞት ነበር።

አውሮፕላኑ በባቡሩ ሐዲዱ ላይ ከወደቀ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ በከፍተኛ ፍጥነት እበረረ የሚመጣ ባቡር ከመድረሱ በፊት ጉዳት ደርሶበት አውሮፕላኑ ውስጥ የነበረውን አብራሪ ማትረፍ እጅግ አስጨናቂ ነበረ።

ነገር ግን በአደጋው ስፍራ የነበሩት የሎስ አንጀለስ ፖሊሶች በነበራቸው ጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ አብራሪውን ከአውሮፕላኑ ውስጥ በማውጣት በባቡር ተገጭቶ ከሚደርስ አሰቃቂ አደጋ አትርፈውታል።

የክስተቱን የመጨረሻዎቹን ሰከንዶች አንድ ግለሰብ በሞባይሉ ቀርጾታል።