የዓለምን ሕዝብ የኮቪድ-19 መከላከያን መከተብ ያልተቻለው ለምንድን ነው?

የተንቀሳቃሹ ምስል መግለጫ, አስካሁን የዓለምን ሕዝብ በሙሉ የኮቪድ-19 መከላከያ መከተብ ያልተቻለው ለምንድን ነው?
ታትሟል

አዲሱ የኮሮናቫይረስ ልውጥ ዝርያ ኦሚክሮን መኖሩ ከታወቀ በኋላ በሁሉም የዓለም አገራት በሚባል ደረጃ ተገኝቶ ወረርሽኙን በፍጥነት እያስፋፋው ይገኛል።

በዚህም ሳቢያ የቫይረሱን ስርጭት ለመቆጣጠር ባለፀጋ አገራት ክትባት በስፋት እየሰጡ ከመሆናቸው በተጨማሪ የማጠናከሪያ ክትባትን ለሕዝባቸው በበቂ ሁኔታ እያቀረቡ ነው።

ከዚህ በተቃራኒ ደግሞ በማደግ ላይ ያሉ አገራት ክትባቱን በሚፈልጉት መጠን ስላላገኙ በበሽታው የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በፍጥነት እየጨመረ፣ የማጠናከሪያ ክትባቱ ቀርቶ የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ዙር ክትባቱን ለሕዝባቸው ለመስጠት ፈተና ገጥሟቸዋል። በዚህም ሳቢያ የክትባት አቅርቦቱ ፍትሃዊ አለመሆን በሽታውን ለመከላከል በሚደረገው ጥረት ላይ እንቅፋት እንደሆነ እየተነገረ ነው።

ክትባቱ በስፋት እየተመረተ ለምን ለሁሉም አገራት በበቂ ሁኔታ ሊዳረስ አልቻለም? ይህስ ችግር እንዴት ሊቀረፍ ይችላል? ይህ ቪዲዮ መልስ ይሰጣል።