የዓለማችን የሜዳ ቴኒስ ኮከብ ራፋኤል ናዳልን የገጠሙት የ97 ዓመቱ አዛውንት
ታትሟል
የሜዳ ቴኒስ ጨዋታን ከነፍሳቸው የሚወዱት ዩክሬናዊው ስታኒስላቭስኪ ለ50 ዓመታት ሜዳ ቴኒስ እየተጫወቱ ቆይተዋል። አሁን ዕድሜያቸው 97 ዓመት ደርሷል።
ነገር ግን አሁንም ጨዋታውን አላቆሙም። ሰሞኑን ከ20 ጊዜ በላይ የዓለማችንን ታላቁን የሜዳ ቴኒስ ውድድርን ካሸነፈው ስፔናዊ ኮከብ ራፋኤል ናዳል ጋር ያደረጉት ጨዋታ በማኅበራዊ ሚዲያ መድረኮች ላይ በእጅጉ መነጋገሪያ ሆኗል።