'በኮሮናቫይረስ ምክንያት የማስታወስ ችሎታዬን አጥቻለሁ'
ታትሟል
በኮሮናቫይረስ ለረጅም ጊዜ ከተሰቃዩ ሚሊዮን የዓለማችን ሰዎች መካከል ሮቼሌ ዴቪድ አንዷ ነች።
ሮቼሌ ከቫይረሱ ካገገመች 10 ወራት ቢቆጠሩም አንድን ነገር ለማስታወስ ከአንድ ክፍል ወደ ሌላ ክፍል እየተራመደች መሆኗን ሐኪሟ ይናገራሉ።
የኮቪድ-19 ሕመም የሚያስከትለው ጉዳት ለረጅም ጊዜ የሚቆይበት አንደኛው ምክንያት ድካም ነው። የራስ ምታት፣ የፀጉር መሳሳት፣ የትኩረት ማጣት፣ ጠረን እና ጣዕም መለየት አለመቻል የመሳሰሉት ምልክቶቹ ናቸው።