የታሊባን መስፋፋትን ለመግታት የአፍጋኒስታን መንግሥት ሰዓት እላፊ ደነገገ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
ታሊባን ከተሞችን እንዳይወሩ ለማስቆም በማሰብ የአፍጋኒስታን መንግሥት ቅዳሜ ዕለት በመላ ሃገሪቱ በሚባል ደረጃለአንድ ወር የሚዘልቅ የሰዓት እላፊ ደነገገ።
የአሜሪካ ጦር ከአፍጋኒስታን መውጣቱን ተከትሎ ባለፉት ሁለት ወራት በታሊባንና በአፍጋኒስታን መንግሥት መካከልውጊያ ተፋልሟል።
ታጣቂ ቡድኑ ግማሽ ያህሉን ግዛቶች ተቆጣጥሯል ተብሎ ይታሰባል።
የአሜሪካ ኃይሎች ለቀው መውጣታቸውን ተከትሎ ታሊባን ድንበሮችን እና የገጠር አካባቢዎችን እንደገናበመቆጣጠር ፈጣን ድሎችን አግኝቷል።
የሰላም ውይይቶች አዝጋሚ መሆን ጦርነቱ እየጨመረ ብዙ ሕዝብ ወደሚኖርባቸው ከተማዎች ሊሸጋገር ይችላል የሚልስጋት አለ።
ይህን ተከትሎም አንድ ከፍተኛ የአሜሪካ አዛዥ ሃገራቸው የአፍጋኒስታን ወታደሮችን በመደገፍ የአየር ድብደባማድረጓን እንደምትቀጥል ገልጸዋል። ጄኔራል ኬኔት ማኬንዚ ታሊባን ወታደራዊ ድሎችን እያስመዘገበ ስለመሆኑአልሸሸጉም።
ነገር ግን ጥቃቶቹ የአሜሪካ ወታደራዊ ተልዕኮ ማብቂያ ከሆነው ከነሐሴ መጨረሻ በኋላ ስለመቀጠሉ አልተናገሩም።
ከዋና ከተማዋ ካቡል እና ከሌሎች ሁለት ግዛቶች በስተቀር የሰዓት እላፊው ከምሽቱ አራት ሰዓት እስከ ሌሊቱ አስርሰዓት ሲቆይ እገዳው ሁሉንም እንቅስቃሴ ይከለክላል።
ታሊባን ወደ ፊት እየገሰገሰ ባለበት በዚህ ሳምንት ከካንዳሃር ከተማ ውጭ ከባድ ግጭቶች ተካሂደዋል።
በምላሹ ሐሙስ ዕለት አሜሪካ በአካባቢው በሚገኙ ታጣቂዎች ላይ የአየር ድብደባ ጀምራለች። አሜሪካ በአፍጋኒስታንያላት ቆይታ ነሐሴ ላይ በይፋ የሚጠናቀቅ በመሆኑ መጪዎቹ ወራት ስጋት ደቅነዋል።
በአሜሪካ መራሹ ጦር እአአ ጥቅምት 2001 ታሊባንን ከስልጣን አወረደ። ቡድኑ ኦሳማ ቢን ላደንን እና ሌሎችመስከረም 11 በአሜሪካ ላይ ከተፈፀመ ጥቃት ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ግለሰቦች እና ቡድኖች ዒላማ ያደረገ ነበር።
ፕሬዝዳንት ባይደን የሃገራቸው ጦር አፍጋኒስታን በምዕራባውያን ላይ የሚያሴሩ የውጭ ጂሃዲስቶች ማዕከል መሆንእንደማትችል በማረጋገጣቸው የአሜሪካ ወታደሮች መውጣታቸው ትክክል ነው ብለዋል።
በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ የአሜሪካ ወታደሮች በአፍጋኒስታን የአሜሪካ ጦር ማዕከል ከሆነውና በአንድ ወቅት በአስርሺህዎች የሚቆጠሩ ወታደሮችን ከያዘው ከባግራም አየር ማረፊያ ያለኮሽታ ለቀዋል።
አንዳንድ የአሜሪካ ተንታኞች ታሊባን በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ ሀገሪቱን ሊቆጣጠር ይችላል ሲኩ ስጋታቸውንአስቀምጠዋል።












