ስለ ደቡብ ሱዳን ልናውቃቸው የሚገቡ አምስት ነገሮች
ታትሟል
የዓለም ወጣቷ አገር ደቡብ ሱዳን እንደ አገር ከተመሰረተች ዘንድሮ 10ኛ ዓመቷን አክብራለች። ለነጻነት ለዓመታት በእርስ በእርስ ጦርነት ስትታመስ የቆችው ደቡብ ሱዳን፣ ነጻነቷን ስታገኝ የጦርነቱ ታሪክ ይቋጫል የሚል ተስፋ ብትሰንቅም በሰላም የቆየችው ግን 2 ዓመታትን ብቻ ነው። አገሪቱ አሁን በሰብዓዊ ቀውስ ውስጥ የምትገኝ ሲሆን ሙሉ በሙሉ አገሪቱ ልትታመስ ይችላል የሚል ስጋት አለ። ነገር ግን ይህች በጦርነት የምትታመሰው አገር ከጦርነት ውጭ የሚነገር ብዙ ነገር አላት። የሚነገሩላት ነገሮች ታዲያ ምንድን ናቸው? ቢቢሲ የተወሰኑትን ዳስሷል።