በጣና ሐይቅ ላይ የተንሰራፋው እምቦጭ አረም ተሸነፈ ወይስ በረታ?
ታትሟል
በኢትዮጵያ ትልቁ የሆነው የጣና ሐይቅ በእምቦጭ ተስፋፊ አረም ሰፊ አካሉ ተሸፍኖ የሐይቁ ህልውና አደጋ ላይ እንደጣለው ለዓመታት ሲነገር ቆይቷል።
በተለያዩ ጊዜያትም የክልሉ መንግሥት፣ ነዋሪዎችና የሐይቁን ደኅንነት ለመጠበቅ ፍላጎት ያላቸው ግለሰቦች አረሙን ለማስወገድ የተለያዩ ጥረቶች ሲያደርጉ ነበር።
ታዲያ በዚህ ሂደት ውስጥ የጣና ሐይቅ ስጋት የሆነው የእምቦጭ አረም ተሸነፈ ወይስ በረታ?
ከሦስት ዓመት በፊት ቢቢሲ ወደስፍራው በማምራት የእንቦጩን ሁኔታ ዘግቦ ነበር። በወቅቱም አረሙ ቢያንስ 50 ሺህ ሄክታር የሐይቁን ስፋት እንደሸፈነ ባለሙያዎች አረጋግጠዋል።
ላለፉት ሁለት ዓመታት በተካሄደው ዘመቻ ደግሞ አብዛኛው የሐይቁ ክፍል ከአረሙ መጽዳቱን በሐይቁ ዙሪያ የሚሰሩ ተቋማት እየተናገሩ ነው። ለመሆኑ አሁን ያለው ሁኔታ ምን ይመስላል? ቢቢሲ በድጋሚ አሁን ያለበት ሁኔታን ተመልከቷል።