ኮሮናቫይረስ፡ ፓኪስታን 'ዜጎቼ የኢድ አል ፈጥርን በዓል ከቤታችሁ ሳትወጡ አክብሩ' ብላለች

የፎቶው ባለመብት, EPA
ከቀናት በኋላ የሚከበረውን የኢድ አል ፈጥር በአል ከግምት ውስጥ በማስገባት ፓኪስታን ለስምንት ቀናት የሚቆይ ከፊል የእንቅስቃሴ ገደብ አስቀምጣለች።
በጣም አስፈላጊ ያልሆኑ የንግድ ተቋማት እና የቱሪዝም መዳረሻዎች እንዲዘጉ የተባለ ሲሆን ከትናንት ሌሊት ጀምሮ ደግሞ በመላው አገሪቱ የትኛውም አይነት ጉዞ በከፊል ክልከላ ተደርጎባቸዋል።
ፓኪስታን በአሁኑ ሰአት ሶስተኛ ዙር የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን እየተዋጋች ነው። ባሳለፍነው ወር ብቻ ደግሞ በአገሪቱከ140 ሺ በላይ ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን 3 ሺ ሰዎች ደግሞ ከወረርሽኙ ጋር በተያያዘ ህይወታቸው አልፏል።
የአገሪቱ ባለስልጣናትም በጎረቤት አገር ሕንድ እየሆነ ያለውን ለተመለከተ ሰው በፓሰኪስታን የተጣለው የእንቅስቃሴ ገደብ አላስፈላጊ እንደሆነ መረዳት ይችላል ብለዋል።
ትናንት ቅዳሜ በፓኪስታን 4 ሺ 109 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን የአገሪቱ ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።
ነገር ግንበአገሪቱ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች በትክክል ሪፖርት ስለማይደረግ ዕለታዊ ቁጥሩ ከሚገለጸውም በላይ እንደሚሆን ተገልጿል።
በአዲሱ የፓኪስታን ግማሽ የእንቅስቃሴ ገደብ መሰረት በጣም አስፈላጊ ከሆኑ ሱቆች በስተቀር በርካታ የገበያ ስፍራዎች ዝግ ሆነው ይቆያሉ።
በከተሞችና ከተማ ወደ ከተማ የሚደረጉ ጉዞዎች በጥብቅ ክትትል እንዲደረጉ የታዘዘ ሲሆን የግል ተሽከርካሪዎች፣ ታክሲዎችና ባቡሮችም ቢሆኑ በተወሰነ ተሳፋሪ ብቻ ይንቀሳቀሳሉ።
ባለስልጣናት የኢድን በአል ተከትሎ ሰዎች ከቦታ ቦታ መንቀሳቀሳቸውና ተሰባስበው በአሉን ማክበራቸው የቫይረሱን ስርጭት በከፍተኛ ሁኔታ እንዳይጨምረው ሰግተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ኢምራን ካሃንን በጤና ጉዳዮች ላይ የሚያማክሩት ዶክተር ፋይሳል ሱልጣን እንደሚሉትበ የተቀደሰው የረመዳን ወር መጠናቀቂያ መቅረቡን ተከትሎ ፓኪስታን ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ አለባት።
‘’ምንም እንኳን በየቀኑ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ መጨመር ቢያቆምም ከበአሉ ጋር ተያይዞ ግን እርምጃካልተወሰደ በርካቶች ሊያዙ ይችላሉ ብለዋል።
ሕንድ በአሁኑ ጊዜ በዓለም ላይ እጅግ በከፋ የኮሮና ቫይረስ ማዕበል ውስጥ ስትሆን በየቀኑ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ በሺዎች የሚቆጠሩ ደግሞ ለህልፈት በመዳረግ ላይ ናቸው።
በርካታ አገራትም ሕንድን ለማገዝእንደ መድሀኒት፣ ኦክስጂን እና ሌሎች መከላከያዎች ያሉ ቁሳቁሶችን ወደአገሪቱ እየላኩ ነው።
የጎረቤት አገር ሕንድ ሁኔታ በዚህ የሚቀጥል ከሆነ ለፓኪስታንም በጣም ያሰጋታል ይላሉ ዶክተር ፋይሳል ሱልጣን።
እንደ ሌላ ጊዜው ቢሆን ኖሮ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የኢድ በአልን ለማክበር ከተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች ወደፓኪስታን ይጓዛሉ። አሁን ግን ፓኪስታን በርካታ አገራት ላይ የጉዞ እግድ አስቀምጣለች።
ከሌሎች አገራት ወደ ፓኪስታን ለሚመጡ ተጓዠች በሚል አገራት በሶስት ተከፍለዋል።
የመጀመሪያው ምንም ስጋርየሌለባቸው አገራት ሲሆን ሁለተኛው የኮቪድ-19 ምርመራ ውጤት የማያስፈልጋቸው አገራት ናቸው።
ሶስተኛው ምድብደግሞ ከፍልተኛ ስጋት ያለባቸው አገራት በሚል ተለይተዋል።














