በሕይወት እያሉ 'ሞታችኋል' ተብለው የጡረታ መብት የተነፈጉት ናይጄሪያዊያን

የተንቀሳቃሹ ምስል መግለጫ, የናይጄሪያ ጡረተኞች 'ሞታችኋል' ተብለው አለመሞታቸውን ለማሳየት እየታገሉ ነው
ታትሟል

በናይጄሪያ በርካታ ጡረተኞች 'ሟች' ተብለው ጡረታቸው ተቋርጧል። በእነርሱ ፋንታ ሐሰተኛ ጡረተኛ በማስገባት ገንዘቡ ይመዘበራል።

የሚገርመው ግን ሞተዋል ከተባሉት መካከል 99 በመቶ የሚሆኑት በሕይወት መኖራቸውን ራሳቸው "ሞታችኋል" የተባሉት ጡረተኞች ይናገራሉ። ጡረተኞቹ የተቋረጠባቸው የጡረታ መብት ለማስከበር ትግል ላይ ናቸው።

ቢቢሲ ሰፊ ጥናት በማድረግ የናይጄሪያ ጡረተኞች የሚንገላቱበትን ብልሹ አሰራር አጋልጧል።