የኢትዮጵያ ባሕል የሚያስተዋውቁት የሞባይል ጨዋታዎች
ታትሟል
ዳዊት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 'በኤሌክትሪካል እና ኮምፒውተር ኢንጅነሪንግ' የተመረቀ ሲሆን የኩኩሉ ጌም ከሀሳብ ወደ ተግባር የተቀየረው የመጨረሻ ዓመት ተማሪ ሳለ ነበር።
የኩኩሉን የመነሻ ውጤትን ይዞ ከሌላ ጓደኛው ጋር በመሆን ያቋቋመው ኩባንያ አሁን አራት ዓመታት አስቆጠሯል። ኩባንያው በአንድ ባለሃብት አማካኝነት የ8.6 ሚሊዮን ብር ኢንቨስትመንት ማግኘቱንም ይናገራል - ዳዊት።