ግብጽ የሱዩዝ ቦይን ዘግታ የነበረችውን መርከብ 900 ሚሊዮን ዶላር ካሳ እንድትከፍል ጠየቀች

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
ባለፈው መጋቢት ወር የሱዩዝ ቦይን መተላለፊያ ዘግታው የነበረችው መረከብ ባለቤት የሆነው የጃፓኑ ተቋም 900 ሚሊዩን ዶላር ካሳ ካልከፈላት መረከቧን ይዛ እንደምትቆይ ግብጽ ገለፀች።
የቦዩ አስተዳደር ጉዳዩ በቀላሉ መፍትሔ እንዲያገኝ ጥያቄ ቢቀርብለትም ሳይቀበለው መቅረቱን ለመርከቧ የመድህን ሽፍን ለሰጡ የኢንሹራንስ ተቋም መካከል አንዱ የሆነው 'ዩኬ ክለብ' የተባለ ገልጿል።
እንደተቋሙ ገለጻ "300 ሚሊዮን ዶላር የጥገና ጉርሻና 300 ሚሊዩን ዶላር ደግሞ የጠፋወን ስሜን ለማደስ የሚለውን ጨምሮ የቀረበው የካሳ ጥያቄ "እጅግ በጣም የበዛና" እና "በአብዛኛው ተቀባይነት የሌለለው" ነው።
'ኤቨር ጊቨንስ' የተሰኘችው መርከብ በዚሁ ጥያቄ ምክንያት በቦዩ መካከለኛ ስፍራ በሚገኝ ሐይቅ ላይ መቋሞ ተዘግቧል።
400 ሜትር የሚረዝመውና 220 ሺህ ቶን የሚመዝንነው መርከቡ እንደ አውሮፓውያኑ መጋቢት 23/2021 ነበር ባጋጠማት የበረታ በአሸዋ የተሞላ ንፋስ አቅጣጫዋን ስታ መንገድ የዘጋችው።
ይህም ለስድስት ቀናት የቦዩን ተግባር አስተጓጉሏል። ከስድስት ቀናት በኋላ ግን በግምት 30 ሺህ ኪዩቢክ ሜትር ጭቃና አሸዋ ተወግዶ መርካቧ የመተላለፊያውን መስመር ለቃ ቦዩ ክፍት ተደርጓል።
ኤቨር ጊቨን መተላለፊያውን በዘጋችበት ወቅት ከ400 በላይ መርከቦች ለቀናት ከመንገዳቸው ተስተጓጉለው ለመቆም ተገደው ነበር።
ሜዲትራኒያንና ቀይ ባሕርን የሚያገናኘው የስዩዝ ቦይ 193 ኪሎ ሜትር የሚረዝም ሲሆን እስያን እና አውሮፓን የሚያስተሳስር አጭሩ የባሕር ማቋረጫ መንገድ ነው።
እናም ግብጽ ደርሶብኛል ላለችው ጉዳት 900 ሚሊዮን ዶላር እንዲከፈላት ብትጠይቅም "ይህ ባለመሆኑ መርከቧ በግብጽ እጅ እንደምትቆይ" የስዩዝ ቦይ አስተዳደር ሊቀ መንበርን ጠቅሶ የግብጽ ብሔራዊ ጣቢያ ዘግቧል።
ይህ የካሳ ክፍያ የገንዘብ መጠን "በቆሙ መርከቦች ኪሳራና የጥገናን ወጪ" መሰረት አድርጎ መሰላቱንም ገልጸዋል።
ከመርከቧ ኢንሹራንስ ሰጪ 'ዩኬ ክለብ' የመሰረተ ልማት ካሳን ክፍያንና የሥራ መስተጓጉል ወጪን ጨምሮ ሌሎች ዋስትናዎችን በሦስተኛ ወገን የተቀበለው ኢንሹራንስ ባለቤት ሾይ ኪሰን ካይሻን "በስምምነት ለመፍታት ከቦዩ አስተዳደር ጋር እየተደራደርን ነው" ብለዋል።
"ባለፈው ሰኞ ጥያቄችንን ለቦዩ አስተዳደር በአግባቡ አቅርበንናል" ያሉት ባለቤቱ "አስተዳደሩ መርከቧን ለመያዝ በመወሰኑ ቅር ተሰኝተናል" ሲልም ገልጿል።
"ካሳው እስኪከፈል በሚል መርከቧንና በውስጧ ያሉ ሠራተኞች በግብጽ እንዲቆዩ መወሰኑ ቅር አሰኝቶናልም" ብሏል።
'ዩኬ ክለብ' በበኩሉ በካሳ ጥያቄው ዙሪያ ዝርዝር ማብራሪያ አላቀረበም ብሏል።













