ለአገራቸው የመጀመሪያውን ከፀሐይ ኃይል ኤሌክትሪክ ማመንጫ ያቋቋሙ ሴቶች
ታትሟል
ለዓመታት በጦርነት እየታመሰች ባለችው የመን ውስጥ የሚኖረው ሕዝብ ዋነኛ የዕለት ከዕለት ጭንቀታቸው ነፍሳቸውን ማዳን ቢሆንም እነዚህ ሴቶች ግን በስጋት ውስጥ ለሚኖረው ሕዝብ ከፀሐይ ኃይል ኤሌክትሪክ እያመነጩ ነው።
በዚህም እነዚህ የመናውያን ሴቶች በአገሪቱ የመጀመሪያ የሆነውን የፀሐይ ኃይል ማመንጫ አቋቁመው በእራሳቸው እያንቀሳቀሱ ነው።