ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
የግዙፉ ሳምሰንግ ኩባንያ ወራሽ በሙስና ታሰሩ
የግዙፉ ሳምሰንግ ኩባንያ ወራሽ ሊ ጃ ዮንግ በሙስና ወንጀል ጥፋተኛ ሆነው በመገኘታቸው 2 ዓመት ተኩል እስር ተፈረደባቸው፡፡
እስሩን የወሰነው የደቡብ ኮሪያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ነው፡፡
ይህ የሊ ክስ ረዥም ጊዜን የወሰደና የቀድሞዋን የአገሪቱን ፕሬዝዳንት ፓርክ ጊየን ሀይን ጭምር ያነካካ ነበር፡፡
ፕሬዝዳንቷ በዚህ የተነሳ በሙስና ከሥልጣናቸው ተነስተው ዘብጥያ መውረዳቸው ይታወሳል፡፡
ሊ ጃ ዮንግ ከ2014 ጀምሮ የሳምሰንግ ወራሽና የሳምሰንግ ኤሌክትሮኒክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆኖ ነው የሚታየው፡፡
አሁን በሙስና መታሰሩ ምናልባት በኩባንያው ውስጥ በሥራ አስፈጻሚነት የመቀጠሉን ነገር ጥያቄ ምልክት ውስጥ የሚያስገባ ነው፡፡
ይህንን ወራሽነት ሥልጣን ሊ የተረከበው ከዝነኛው አባቱ ሊ ኩን ሂ በፈረንጆች 2014 የእርሳቸውን መሞት ተከትሎ ነበር፡፡
የሊ አባት በደቡብ ኮሪያ የናጠጡ ቁጥር አንድ ቢሊየነር ነበሩ፡፡
ያን ጊዜ በድምር የ16 ቢሊዮን ዶላር ሐብት በማጋበስ በፎርብስ የሞጃዎች ዝርዝር ቁጥር አንዱ ቢሊየነር ሆነው ነበር የሞቱት፡፡
ለሕዝብ እምብዛምም የማይታዩትና ሚዲያ የማይወዱት የሊ ጃ ዮንግ አባት በ2014 ከዚህ ዓለም በሞት ሲለዩ 78 ዓመታቸው ነበር፡፡
አሁን በሙስና መታሰሩ ምናልባት በኩባንያው ውስጥ በሥራ አስፈጻሚነት የመቀጠሉን ነገር ጥያቄ ምልክት ውስጥ የሚያስገባ ነው፡፡
ይህንን ወራሽነት ሥልጣን ሊ የተረከበው ከዝነኛው አባቱ ሊ ኩን ሂ በፈረንጆች 2014 የእርሳቸውን መሞት ተከትሎ ነበር፡፡
የሊ አባት በደቡብ ኮሪያ የናጠጡ ቁጥር አንድ ቢሊየነር ነበሩ፡፡
ያን ጊዜ በድምር የ16 ቢሊዮን ዶላር ሐብት በማጋበስ በፎርብስ የሞጃዎች ዝርዝር ቁጥር አንዱ ቢሊየነር ሆነው ነበር የሞቱት፡፡
ለሕዝብ እምብዛምም የማይታዩትና ሚዲያ የማይወዱት የሊ ጃ ዮንግ አባት በ2014 ከዚህ ዓለም በሞት ሲለዩ 78 ዓመታቸው ነበር፡፡
ሳምሰንግ ግሩፕ የኢንሹራንስ፣ የሳምሰንግ ኢንዱስትሪና የሳምሰንግ ሲ ኤንድ ቲ እንዲሁም ሌሎች በርካታ እህት ኩባንያዎች ያሉት ሲሆን የበርካታ አሜሪካና የደቡብ ኮሪያ ኩባንያዎች ድርሻ ያለው ንብረት ነው፡፡
ይሁን እንጂ ብልጹጉ የሊ ቤተሰብ በኩባንያው ላይ ከፍተኛ ድርሻና ውሳኔን የማስቀልበስ ድምጽ በግዙፉ የሳምሰንግ ኢንሹራንሱ በኩል እንደያዙ አሉ፡፡
የሳምሰንግ ኤሌክትሮኒክስን ከትንሽ አንስተው የዓለም ቁንጮ ኩባንያ ያደረጉትም ሊ ኩን ሂ ነበሩ፡፡
ሳምሰንግ ኩባንያ ከቤተሰብ ሲወራረድ አሁን የታሰሩት ሊ ጃ ዩንግ 4ኛ ትውልድ ናቸው፡፡
ኩባንያው የተመሰረተው እንደ አውሮፓዊያኑ በ1938 በጣም ትንሽ ሱቅ ሆኖ በ30 ዶላር ነበር፡፡
የሊ ጃ ዮንግ አባት ሊ ኩን ሒ በለውጥ የሚያምኑና ተራማጅ ነበሩ፡፡
‹‹ከሚስቶቻችንና ከልጆቻችን ውጭ ሁሉምን ነገር መቀየር ያሻል›› የሚል ፍልስፍና ነበራቸው፡፡
በ1993 ሊ ኩን ሒ በመጋዘን የሚገኙ 150ሺህ ፋሽን ያለፈባቸውን ስልኮችን በማቃጠል አዲስ ምርቶችን ወደ ገበያ በማውጣት የለውጥ ሰው መሆናቸውን አስመስክረዋል፡፡
ልጃቸው ሊ በ2017 ተከሶ ጥፋተኛ ተብሎ ነበር፡፡
ይህም ከፕሬዝዳንቷ ጋር በሙስና ተዛምደሀል፣ ለፕሬዝዳንቷ የቅርብ ጓደኛ ድርጅት የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ የፕሬዝዳንት ፓርክን መንግሥት ለማማለል ሞክረሃል በሚል ነበር፡፡
ሆኖም በይግባኝ የእስር ውሳኔው እንዲዘገይ ሆኖለታል፡፡
ሳምሰንግ ለሁለት ለትርፍ ያልተቋቋሙ ድርጅቶች የ37 ሚሊዮን ዶላር ልገሳ አድርጎ ነበር ያኔ፡፡
ልገሳው የተደረገላቸውን ድርጅቶች የሚመሩት ደግሞ ቾን ሱን ሲል ነበሩ፡፡ ቾይ ደግሞ የፕሬዝዳንት ፓርክ የቅርብ ጓደኛ እንደሆኑ ይታወቃል፡፡
በዚህ የተነሳ ሳምሰንግ ከደቡብ ኮሪያ መንግሥት የእጅ አዙር ድጋፍ እንዲያገኝ አስችሎታል በሚል ክስ ተመስርቶበት ፕሬዝዳንቷንም ከሥልጣን ያስነሳ ትልቅ የሙስና ቅሌት ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
ሊ በበኩሉ እኔ ድርጊቱን የፈጸምኩት በበጎ ፈቃድ እንጂ የእጅ አዙር የመንግሥት ድጋፍ ፈልጌ አይደለም ብሎ ተከራክሯል፡፡
ይህን ተከትሎ በነሐሴ 2017 ፍርድ ቤት 5 ዓመት እስር ፈርዶበት ዘብጥያ ቢወረውረውም ፍርዱ በይግባኝ ተቀንሶለት በየካቲት 2018 ነጻ ተብሎ ነበር፡፡
ሆኖም ከፍተኛው የሲዮል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በእንጥልጥል የቆየውን ፍርዱን ዛሬ ሰኞ አጽንቶበት ነው ሊ ወደ ወህኒ የገባው፡፡