የኡጋንዳ ምርጫ 2021 ፡ የኡጋንዳን ምርጫ ለመረዳት የሚያግዙ አምሰት ዋና ዋና ጉዳዮች
ታትሟል
ኡጋንዳ ሐሙስ ጥር 06/2013 ምርጫ አካሂዳለች። በምርጫው አገሪቱን ለ34 ዓመታት የመሩት ዩዌሪ ካጉታ ሙሴቬኒ እና ሙዚቀኛው ቦቢ ዋይን ዋነኞቹ ተፎካካሪዎች ናቸው።
በኡጋንዳ ወጣቶች ከፍተኛ የፖለቲካ ተሳትፎ አላቸው። እናም የወጣቶቹን ድጋፍ ለማግኘት ሁለቱም ተፎካካሪዎች ብርቱ ውድድር እያደረጉ ነው።
ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሞሴቬኒ ጠንካራ ወታደራዊ ኃይል በመገንባት ኡጋንዳን በምሥራቅ አፍሪካ ተጽዕኖ ፈጣሪ አገር ለማድረግ ቃል ገብተዋል። በሌላ በኩል ቦቢ ዋይን በአገሪቱ ሥር የሰደደውን የወጣቶች ሥራ አጥነት ለመቀነስ እሰራለሁ ብሏል።
ከምርጫው በፊት በመንግሥት ላይ በተቀሰቀሱ በተደጋጋሚ ተቃውሞዎች ከ50 በላይ ሰዎች ተገድለዋል። የምርጫው ውጤትስ በምን ሁኔታ ይቋጭ ይሆን? ብዙዎች አለመረጋጋት ሊከሰት ይችላል በሚል ስጋት ላይ ናቸው።