መሪ ለመሆን በኒው ዮርክ ከሚሰለጥኑት አፍሪካውያን መካከል አንዷ የሆነቸው ጫልቱ ዳንኤል
ታትሟል
ጫልቱ ዳንኤል የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም እና የአፍሪካ ሕብረት ባዘጋጁት የመሪነት ስልጠና ከኢትዮጵያ ተመርጣ በተባበሩት መንግሥታት ዋና መቀመጫ በሆነችው ኒው ዮርክ የመሪነት ስልጠና እየወሰደች ትገኛለች። ከተለያዩ አገራት ከተውጣጡ ሰዎች ጋር የምታደርገው የመሪነት ስልጠና ልዩ እውቀት እንደጨመረላት የምትናገረው ጫልቱ በቀጣይ ከአገሯ ባለፈ በአፍሪካ እና በዓለም ዙሪያ የመሪነት ሚና ለመጫወት እየተጋች ትገኛለች።