ኮቪድ-19 በፍጥነት ዓለምን ያዳረሰበት ምክንያት ምንድን ነው?
ታትሟል
ኮቪድ-19 አንድ ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ መላው ዓለምን አዳርሶ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሰዎችን ለሞት ዳርጓል። ከ40 ሚሊዮን በላይ ሰዎችም በቫይረሱ ተይዘዋል። ኮቪድ-19 ዓለምን ያዳርስ እንጅ ከአሁን በፊት ተከስተው ከነበሩት ሳርስ እና ሜርስ ኮሮናቫይረሶች አንጻር ሲታይ ገዳይነቱ አናሳ ነው። በአንጻሩ የስርጭት ፍጥነቱ ደግሞ እጅግ ፈጣን ነው። ለምን?