"ሲድኒ ላይ ያሸነፈው የእግዚአብሔር እግር ነው"- ኃይሌ ገብረ ሥላሴ

የተንቀሳቃሹ ምስል መግለጫ, ሲዲኒ ላይ ያሸነፈው የእግዚኣብሔር እግር ነው፡ አትሌት ኃይሌ ገብረ ሥላሴ።
ታትሟል

አትሌት ኃይሌ ገብረ ሥላሴ የምንጊዜም ታላቅ ሯጭ ነው። ከትራክ እስከ ጎዳና ላይ ውድድሮች ኢትዮጵያዊው ጀግና ክብረ ወሰኖችን እየሰባበረ በሁሉም ድልን ተቀዳጅቶባቸዋል። ኃይሌ ባደረጋቸው ውድድሮች፣ 2 የኦሊምፒክ የወርቅ ሜዳሊያ፣ 4 የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮናነትን እና 4 የቤት ውስጥ ውድድሮችን አሸንፏል̀። 27 ክብረ ወሰኖችን ሰባብሯል። ነገር ግን ለኃይሌ የትኛው ይበልጥበታል? የታላቁ ሯጭ አምስቱ ምርጫዎች እነዚህ ናቸው!