ሜክሲኮ ስደተኛ ዜጎቼን አሜሪካ "አምክናለች" በማለት ምርመራ ጀመረች

የፎቶው ባለመብት, Karen Ducey
በአሜሪካ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ውስጥ ስድስት የሜክሲኮ ስደተኞች በህክምና መክነዋል የሚለውን ክስ ተከትሎ ሜክሲኮ ምርመራ መጀመሯን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ማርሴሊ ኤብራርድ አስታውቀዋል።
ይህንን ያጋለጠችው ነርስ ባለፈው ሳምንት በስደተኛ ሴቶች ላይ ያለ ፈቃዳቸው ማህፀናቸው በህክምና እንዲወገድ (ሂስትሬክቶሚ) ተደርጓል ተብሏል።
በአይስ ቁጥጥር ስር የዋሉ ስደተኛ ሴቶች ጆርጂያ ግዛት በሚገኘው የመጠለያ ማእከል በህክምና እንዲመክኑ ተደርገዋል ተብሏል።
ይህንን ያጋለጠችው በማእከሉ የምትሰራ ዳውን ውተን የተባለ ነርስ ሲሆን በርካታ ሴቶችም ማሕፀናቸው በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ እንዲወገድ ተደርጓል ብላለች።
የአሜሪካ የስደተኞች ባለስልጣናት በበኩላቸው ይህንን ውንጀላ በጥብቅ እንደሚያዩት አስረድተዋል።
ሜክሲኮ ይህንን ተልዕኮ "ተቀባይነት የለውም" ብላለች
"መክነዋል የተባሉና ማህፀናቸው እንዲወገድ የተደረጉ ስድስት ሴቶችን ስለ ሁኔታው እየጠየቅናቸው ነው" በማለት ሚኒስትሩ ትናንት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል።
"በርግጠኝነት እውነት ሆኖ ከተገኘ በቀላሉ የምናየው አይሆንም እርምጃም የምንወስድ ይሆናል" ብለዋል።
የአገሪቱ ፕሬዚዳንት አንድሬስ ማኑኤል ሎፔዝ ኦብራዶም በበኩላቸው የማምከኑ ነገር እውነት ተፈፅሞ ከሆነ አገራቸው ህጋዊ እርምጃን እንደምትወስድም የሜክሲኮው ጋዜጣ ኤል ዩኒቨርሳል ሰኞ እለት ባወጣው እትም አስነብቧል።
ከ150 በላይ የሚሆኑ የአሜሪካ የምክር ቤት አባላትም መጠለያ ማዕከሉ ላይ ምርመራ እንዲከፈት ጥሪ አቅርበዋል።
ሆኖም የመጠለያ ማዕከሉም ሆነ የኢሚግሬሽን ባለስልጣኑ ድርጅት 'አይስ "ይህ ያልተረጋገጠ ውንጀላ ነው። እስካሁን ምንም መረጃም ስለሌለ በጥርጣሬ ነው መታየት ያለበት" በማለት ለቢቢሲ አስረድቷል።
የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ቡድኖችም የግል ይዞታ የሆነውና አርዊን የተባለው መጠለያ ማዕከሉም ላይ ክስ እንከፍታለን ብሏል።
ዳውንና ሌሎች ነርሶች በርካታ ሴቶች ማህፀን አለመኖሩ እንዳስደነገጣቸውም መናገራቸውን ቡድኑ ገልጿል።
ዳውን እንደምትለው አንደኛው ዶክተር የእንቁላል አምራች ክፍል እንቁልጢ (ኦቫሪን) ታዳጊ ከሆነች ስደተኛ በቀዶ ህክምና ሲያስወጣ ያየች ሲሆን ሁሉም በሚባል ሁኔታ ማህፀናቸው እንደተቆረጠም ማየት ችላች።
"የሁሉንም ማሕፀን እያወጣ ነው ብለን እርስ በርስ መጠያየቅ ጀመርን። የሱ ሙያም ነው፣ የማህፀን ሰብሳቢም አልነው" በማለትም ባቀረበችው ሪፖርት ላይ አስፍራለች።
አንደኛዋ የማዕከሉ ስደተኛ በበኩሏ "ሙከራ የሚደረግበት የግዞት መጠለያ ነው። በስውነታችን ላይ እየሞከሩብን ነው" ብላለች።
ማዕከሉን የሚመራው ላዛሌ ኮሬክሽን የተባለው ኩባንያ ፍፁም ውንጀላ ነው በማለት ማጣጣሉን አሶሺየትድ ፕሬስ ዘግቧል።












