እስር ቤት እያለሁ ኮሮናቫይረስ ሲገኝብኝ የምሞት መስሎኝ ነበር-ያሲን ጁማ

የተንቀሳቃሹ ምስል መግለጫ, ያለጥፋቴ ታስሬ በዚያ ላይ ኮሮናቫይረስ ሲገኝብኝ እዚያው እስር ቤት ውስጥ የምሞት መስሎኝ ነበር፡ ያሲን ጁማ
ታትሟል

ከአርቲስት ሃጫሉ ግድያ በኋላ በርካታ ሰዎች መታሰራቸው ይታወሳል። በወቅቱ በተለያዩ ወንጀሎች ተጠርጥረው ታስረው ከነበሩት ሰዎች መካከል ኬንያዊው ጋዜጠኛ ያሲን ጁማ አንዱ ነው። ያሲን ጁማ እስር ቤት በነበረበት ወቅት የኮሮናቫይረስ ታሞ በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ማገገም ችሏል። በተከሰሰበት ወንጀልም ነጻ ተብሎ ወደ አገሩ ኬንያ በመመለስ አሁን ከቤተሰቦቹ ጋር ናይሮቢ ይገኛል። ከቢቢሲ ጋር ቆይታ ያደረገው ያሲን "ያለጥፋቴ ታስሬ፣ በዚያ ላይ ኮሮናቫይረስ ሲገኝብኝ እዚያው እስር ቤት ውስጥ የምሞት መስሎኝ ነበር" በማለት የነበረውን ሁኔታ ይገልጻል።