ሜክሲኮ ውስጥ የጎብኚዋን ፀጉር አሸተተ የተባለው ድብ እንዲኮላሸ ተደረገ

A black bear paws at a women's calf
ታትሟል

ሜክሲኮ ውስጥ የአንዲት ጎብኚን ፀጉር አሽትቷል የተባለው ጥቁር ድብ ተይዞ መኮላሸቱ ቁጣ ቀስቅሷል።

ጥቁሩ ድብ ፓርክ ውስጥ ለጉብኝት የመጣችን ሴት ፀጉር ሲያሸት በተንቀሳቃሽ ስልክ መቀረፁን ተከትሎ ነው የፓርኩ ሰዎች ድቡን ያኮላሹት።

ጎብኝዎች ድቡን ከማኮላሸት ይልቅ ወደ ሌላ የእንስሳት ማቆያ መውሰድ አይሻልም ወይ? ሲሉ ይጠይቃሉ። ነገር ግን ባለሙያዎች ድቡ ከሰዎች እጅ ምግብ መብላት በመልመዱ ሌላ ቦታ ሄዶ መኖር ይከብደዋል ይላሉ።

96 ኪሎግራም የሚመዝነው ታዳጊው ጥቁር ድብ ጎብኚዎችን አደጋ ላይ ይጥላል በሚል ነው በፓርኩ ሰዎች እርምጃ የተወሰደበት።

ጎብኚዋ ከድቡ ጋር ራሷን ፎቶ ልታነሳ ስትቀርበው ነው ጎተት አደርጎ የፀጉሯን መዓዛ አሸተተ የተባለው። ምንም እንኳ ድቡ ወጣቷ ጎብኚ ላይ ጉዳት ባያደርስም ለወደፊቱ የሚመጣ ጉዳትን በመፍራት ነው የፓርኩ ሰዎች ከዚህ ውሳኔ ላይ የደርስነው ይላሉ።

የፓርኩ ሰዎች ከዚህ በፊትም ይህ ታዳጊ ድብ ከሰዎች ጋር በቅርብ ርቀት ታይቷል፤ ከሰዎች እጅ ምግብ መብላት ለምዷል ይላሉ።

ጎብኝዎች 'ቺፒ' እያሉ የሚጠሩት ድብ ፓርኩ አካባቢ በሚኖሩ ሰዎች ዘንድም ይወደዳል።

ድቡ አሁን ወደ ሚኖርበት ፓርክ የመጣው ከአንድ መኖሪያ ቤት ጀርባ እንቅልፉን እየለጠጠ ሳለ የተመለከቱ ነዋሪዎች ለባለሥልጣናት በመጠቆማቸው ነው።

ድቡ መኮለሸቱን ተከትሎ የእንስሳት መብት ተሟጋቾች ምርምራ ይካሄድ እያሉ ነው።

ጎብኚዎችም ሆኑ የአካባቢው ነዋሪዎች ድቡ መኮላሸቱን ተከትሎ ቁጣቸውን ያሰሙ ሲሆን ወደ ሌላ ፓርክ መወሰድ የለበትም የሚሉም አልጠፉም።

ባለሙያዎች ጎብኚዎች ለእንስሳት ምግብ ማስለመዳቸው ነው ለዚህ የዳረገው ይላሉ።

ቺዋዋ የተሰኘችው የሜክሲኮ ግዛት ውስጥ የሚገኘው ሲዬራ ዴ ኒዶ ተራራ የጥቁር ድቦች መናኸሪያ ነው።

የተንቀሳቃሹ ምስል መግለጫ, ከዓለማችን ላይ ሊጠፉ የተቃረቡ 5ቱ እንስሳት የትኛዎቹ ናቸው?