ቤይሩት ፡ አስደንጋጩ ፍንዳታ በተከሰተበት ወቅት የተወለደው ህጻን
ታትሟል
የቤይሩቱ ፍንዳታ ሲከሰት አንዲት እናት ልጇን ለመውለድ ሆስፒታል ገብታ፣ በሐኪሞች እየታገዘች ነበር። ነገር ግን ምጥ ላይ ያለችው እናት ያለችበትን ጨምሮ በርካታ ሕንጻዎች በተፈጠረው አስደንጋጭ ፍንዳታ ምክንያት መፈራረስ ጀመሩ።
እናት በዚህ ከተማዋን ባናወጠው አስደንጋጭ ሁኔታ ውስጥ ሆና ልጇን ለመውለድ በምጥ እየተጨነቀች ነበር። ዕድለኛም ሁና እናት ልጇን በሰላም መውለድ ችላለች።