በሞቃዲሹ ያጋጠመው ፍንዳታ 8 ሰዎችን ገደለ

ታትሟል

በሶማሊያ መዲና ሞቃዲሹ የጦር ካምፕ አቅራቢያ ባጋጠመ ፍንዳታ 8 ሰዎችን መገደላቸውን እና 14 ሰዎች ላይ ጉደት መድረሱን የሶማሊያ ጦር ኃላፊ ተናገረዋል።

ኮሎኑል አህመድ ሙሴ ለአሶሺዬትድ ፕሬስ እንደተናገሩት ፍንዳታው ያጋጠመው በቅርቡ የተከፈተ ስታዲየም አቅራቢያ በሚገኘው የሶማሊያ ጦር 12ኛ ብርጌድ ላይ ነው።

እስከ አሁን ድረስ በሞቃዲሹ ላጋጠመው ፍንዳታ ምክንያት ምን እንደሆነ በይፋ አልተገለጸም።

ይሁን እንጂ የሶማሊያ መገናኛ ብዙሃን የዓይን እማኞችን ዋቢ በማድረግ እንደዘገቡት ከሆነ፤ ስታዲየም አቅራቢያ በሚገኘው የጦር ካምፕ አቅራቢ መኪና ላይ የተጠመደ ቦምብ ጥቃት አድርሷል።

ዳለሳን የተባለው ራዲዮ የፍንዳታው ድምጽ ከየትኛውም የከፍል ይሰማ ነበር ሲል ዘግቧል።

የዓይን እማኞች ለሬውተርስ እንደተናገሩት ፍንዳታው ካጋጠመ በኋላ የሶማሊያ ወታደሮች ተኩስ ከፍተው ነበር።

መቀመጫውን ሱማሊያ ያደረገው ጽንፈኛው ቡድን አልሸባብ ከዚህ ቀደም የጦር ካምፖችን እና የመንግሥት ባለስልጣናት ላይ ዒላማ ያደረጉ ጥቃቶችን በመሰንዘር ይታወቃል።

በዚህም ለጥቃቱ አል-ሸባብን ተጠያቂ ያደረጉ አልታጡም።

በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ ወደ አንድ የገበያ ማዕከል ሊገባ የሞከረን አጥፍቶ ጠፊ ለማስቆም የሞከሩ ሁለት ጥበቆች፤ አጥፍቶ ጠፊው እራሱን አጥፍቶ ጠበቆቹንም ገድሏል።