"እቅዴ በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት አሁን ያለኝን 3 ሺህ ሰራተኛ 6 ሺህ ማድረስ ነበር፤ ግን ቀነሱብኝ"

የተንቀሳቃሹ ምስል መግለጫ, "እቅዴ በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት አሁን ያለኝመን 3 ሺህ ሰራተኛ 6 ሺህ ማድረስ ነበር፤ ግን ቀነሱብኝ"
ታትሟል

ከሳምንታት በፊት በአንዳንድ የኦሮሚያ ክልል አካባቢዎች ተከስቶ የነበረው አለመረጋጋት ከ167 በላይ ሰዎች ህይወት መጥፋት ምክንያት መሆኑ ይታወሳል። ከዚህ ባሻገርም በርካታ ተቋማትና መኖሪያ ቤቶች ላይ በተፈጸመው ጥቃት ከፍተኛ ውድመት መድረሱም ተገልጿል።

በሻሸመኔና በባቱ ከተሞች ውስጥ በተፈጸመው ጥቃት፤ በንብረት ላይ የደረሰው ውድመት ከፍተኛ መሆኑን ቢቢሲ ያናገራቸው የከተማዋ ነዋሪዎችና ባለንብረቶች እማኝነታቸውን ሰጥተዋል።

በእነዚህ ከተሞች ከወደሙ ንብረቶች መካከል በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በዓለማችን የሩጫ ታሪክ ውስጥ ስማቸው ከሚጠቀሱ ጥቂት ብርቅዬ አትሌቶች መካከል አንዱ የሆነው የአትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴ ሁለት ትልልቅ ሆቴሎች ይገኙበታል። "ትክክለኛ ቁጥሩን አላወቅንም፤ እስከ 290 ሚሊዮን [ሊደርስ ይችላል]። እንዲሁ ከሁለት መቶ ሚሊዮን ብር በላይ ብለን ነው የያዝነው" ሲል ለቢቢሲ ተናግሯል።