ሳኡዲ አረቢያ፡ በእስር ላይ የሚገኙት መኪና የማሽከርከር መብት ጠያቂዎች
ታትሟል
እንደ አውሮፓዊያኑ በ2018 የሳኡዲ አረቢያው አልጋ ወራሽ ሞሐመድ ቢን ሳልማን በአገሪቱ ሴቶች መኪና እንዲያሽከረክሩ የሚከለክለውን ሕግ በማንሳታቸው በብዙዎች ዘንድ አድናቆትን አስገኝቶላቸው ነበር።
ነገር ግን ይህ መብት እውን እንዲሆን ሲታገሉ የነበሩት የሳኡዲ አረቢያ የሴቶች መብት ተከራካሪዎች ወደ እስር ቤት ተግዘው ሰቆቃ እንደተፈጸመባቸው ይነገራል።
አልጋ ወራሹ ለውጥ ለማምጣት ከወሰኑ ሁለት ዓመታት ቢቆጠሩም የመብት ጥያቄ አንስተው ለእስር የተዳረጉት የሳኡዲ ዜጎች ግን አሁን ድረስ እስር ቤት ይገኛሉ።