"ኢንተርኔት የዘመናችን ስጦታ በአግባቡ ካልተጠቀምንበት ደግሞ አደጋም ነው" ዶ/ር ጋሻው አብዛ

የተንቀሳቃሹ ምስል መግለጫ, "ኢንተርኔት የዘመናችን ስጡታ በአግባቡ ካልተጠቀምንበት ደግሞ አደጋም ነው" ዶ/ር ጋሻው አብዛ
ታትሟል

ዶክተር ጋሻው አብዛ በአሜሪካ አገር ታውሰን ዩኒቨርሲቲ የስፖርት አስተማሪና ተመራማሪ ናቸው። በተጓዳኝ ደግሞ የታላቁ አፍሪካ ሩጫ መስራችና አባል ናቸው። በዘንድሮው ዓመት የታሰበውን የታላቁ አፍሪካ ሩጫ በአካል ማካሄድ ባለመቻሉ እንደ ደራርቱ ቱሉ እና ቀነኒሳ በቀለ የመሳሰሉ አትሌቶችን በማሳተፍ በዙም ሩጫ አካሂደዋል። ወረርሽኙ ያመጣውን የእንቅስቃሴ ገደብ በኢንተርኔት በመታገዝ ሌሎች ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮችን በቀላሉ መከወን እየተቻለ በመሆኑ "ኢንተርኔት የዘመናችን ስጦታ ነው፤ በአግባቡ ካልተጠቀምንበት ደግሞ አደጋም ነው" ይላሉ።