ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
የኮሮናቫይረስ ክትባትን መቼ እንጠብቅ?
ታትሟል
ሳይንቲስቶች ለኮሮናቫይረስ ክትባት ለማግኘት እየተረባረቡ መሆናቸውን የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል። በመላው ዓለምም ከ70 በላይ የተመራማሪዎች ቡድን ጥረት እያደረገ ይገኛል። አንዳንዶቹ ሙከራቸውን ከእንስሳት ባለፈ በሰው ላይም አድርገው ውጤቱን እየጠበቁ ነው። ብዙ ተስፋ ሰጪ ሂደቶች መኖራቸውም ይነገራል።
ይህ ከሆነ ታዲያ የኮሮናቫይረስ ክትባት ተገኝቶና በበቂ ሁኔታ ተመርቶ የዓለም ሕዝብ ከዚህ አስፈሪ ጭንቀት የሚገላገለው መቼ ነው?