የኮሮናቫይረስ ክትባትን መቼ እንጠብቅ?

የተንቀሳቃሹ ምስል መግለጫ, የኮሮናቫይረስ ክትባት ተገኝቶና በበቂ ሁኔታ ተመርቶ የዓለም ሕዝብ ከዚህ አስፈሪ ጭንቀት የሚገላገለው መቼ ነው?
ታትሟል

ሳይንቲስቶች ለኮሮናቫይረስ ክትባት ለማግኘት እየተረባረቡ መሆናቸውን የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል። በመላው ዓለምም ከ70 በላይ የተመራማሪዎች ቡድን ጥረት እያደረገ ይገኛል። አንዳንዶቹ ሙከራቸውን ከእንስሳት ባለፈ በሰው ላይም አድርገው ውጤቱን እየጠበቁ ነው። ብዙ ተስፋ ሰጪ ሂደቶች መኖራቸውም ይነገራል።

ይህ ከሆነ ታዲያ የኮሮናቫይረስ ክትባት ተገኝቶና በበቂ ሁኔታ ተመርቶ የዓለም ሕዝብ ከዚህ አስፈሪ ጭንቀት የሚገላገለው መቼ ነው?