ኮሮናቫይረስ የቀሰቀሳቸው የአና የሚበሉ ሥዕሎች
ታትሟል
አና ሆይኒትዝካ ለ4 ዓመታት ኢትዮጵያ ከኖረች በኋላ ወደ ትውልድ አገሯ እንግሊዝ የተመለሰችው ከጥቂት ወራት በፊት ነበረ። እርሷ ከወራት በፊት ከኢትዮጵያ ትውጣ እንጂ "ኢትዮጵያ ከውስጤ አልወጣችም" የምትለው አና ትንሽ ከባህሉም ትንሽ ትንሽ ደግሞ ከቋንቋው በውስጧ እንዲቀር አሁንም ጥረት እያደረገች ነው።
አና ባለፈው ሚያዚያ ወር የተከበረውን የፋሲካ በዓል ባታከብረውም እንኳ 'ጣፋጭ' የምትላቸውን ጊዜያት አብሬያቸው አሳልፌያለው የምትላቸውን ጓድኞቿን በማሰብ፤ በግሏ ማኅበራዊ ድረ ግፅ ላይ መልካም ምኞቷን ገልጻላቸዋልች፤ ለዚያውም ባልተለመደ ሁኔታ በሙዝ ላይ የመስቀል ስዕል ሰርታ በአማርኛ 'መልካም ፋሲካ' በማለት።
አና በሙዝ ላይ ስዕል መሳል የጀመረችው ግን ሙዝ መመገብ አስጠልቷት ወይንም በጥበብ ጎዳና ተመርታ ልዩ ሥራ በማቅረብ ፍላጎት ተነሳስታ አልነበረም። አና ከወር በፊት የኮሮናቫይረስ ምልክቶች ታይተውባት ለ10 ቀናት በመኝታ ቤቷ እራሷን አግልላ በቆየችበት ወቅት ነው።