ኮሮናቫይረስ፡ "ሁኔታዎች በዚህ ከቀጠሉ በርሃብ ልናልቅ ነው"
ታትሟል
የኮቪድ-19ን ስርጭት ለመግታት አንዳንድ አገራት እንቅስቃሴን ሙሉ በሙሉ መዝጋትን አማራጭ አድርገዋል።
በእነዚህ አገራት የቫይረሱ ስርጭት በአንጻራዊ ሁኔታ መገታቱ እንዳለ ሆኖ ዜጎቻቸው ግን በርሃብ አለቅን እያሉ ነው።
በተለይ ኑሯቸው ከእጅ ወደ አፍ የሆኑ የዜጎች የገቢ ምንጭ ሙሉ በሙሉ በመድረቁና የመንግሥታት ድጋፍም ዝቅተኛ በመሆኑ ችግር ላይ መውደቃቸውን ይገልጻሉ።
በተመሳሳይ ዓለም አቀፉ የሰራተኞች ድርጅት ከአንድ ነጥብ ስድስት ቢሊዮን በላይ ሰዎች በወረርሽኙ ሳቢያ ከሥራቸው እንደሚፈናቀሉ አስታውቋል።