"ከ80 ሚሊዮን ሕዝቦቼ በድህነት የሚኖሩት 17ቱ ብቻ ናቸው" የቻይናዋ ግዛት

ቻይና ድህነት

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

ታትሟል

የቻይናዋ ጂአንግሱ ግዛት ከ80 ሚሊዮን ነዋሪዎቼ በደህነት የሚኖሩት 17 ሰዎች ብቻ ናቸው አለች።

የግዛቷ አስተዳዳሪዎች በግዛቷ ውስጥ በዓመት ከ863 ዶላር በታች (26ሺህ ብር ገደማ) የሚያገኙት ሰዎች ቁጥር 17 ብቻ ናቸው ብለዋል።

ይህን ማሳካት የተቻለው መንግሥት ሁሉንም ተደራሽ የሚያደርጉ ውጤታማ ሥራዎችን ማከናወን በመቻሉ ነው ተብሏል።

በፈረንጆቹ 2019 ማጠናቀቂያ ላይ የተገኙ አሃዞች እንደሚጠቁሙት፤ ባለፉት አራት ዓመታት 2.54 ሚሊዮን የጂአንግሱ ግዛት ነዋሪዎችን ከድህነት አረንቋ ማውጣት ተችሏል።

ግዛቷ በፈረንጆቹ 2020 ድህነትን ሙሉ ለሙሉ ለማስወገድ አቅዳ ስትንቀሳቀስ ነበር።

አሁንም በድህነት ውስጥ ነው የሚኖሩት የተባሉት 17ቱ ሰዎች፤ ተቀጥሮ ለመስራት የሚያስችል አቅም እንዳላቸው የግዛቷ ባለሥልጣናት ተናግረዋል።

ምንም እንኳን ቻይና ባለፉት ጥቂት አስርተ ዓመታት ኢኮኖሚዋ በፍጥነት ቢያድግም የተፈለገውን ያህል ድህነትን ከመላው ቻይና ማስወገድ አልተቻለም።

ይልቁንም በድሆች እና በባለጠጎች መካከል ያለው ልዩነት እጅጉን ሰፍቶ ቆይቷል።

በዚህም የቻይና መንግሥት ድህነትን ከቻይና ማራቅ የሚለው ዓላማው ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ሆኗል።

በቻይና 'ድህነት' ለሚለው ቃል በትክክል የሚያግባባ ትርጓሜ ማግኘት አስቸጋሪ ነው። የቻይና ግዛቶች ለድህነት የሚሰጡት ትርጓሜ እንደየደረጃቸው ይለያያል።

በሃገር አቀፍ ደረጃ በዓመት ከ331 ዶላር በታች የሚያገኝ ዜጋ ድሃ ተብሎ ይፈረጃል።

እንደ ጂአንግሱ ግዛት ያሉ ደግሞ ነዋሪያቸውን ድሃ የሚሉት በዓመት ከ863 ዶላር በታች የሚያገኝ ከሆነ ነው።

Presentational grey line
የተንቀሳቃሹ ምስል መግለጫ, ለኑሮ ምቹ ከተሞች