በፓሪስ የአንበሳ ደቦሏ ላምቦርጊኒ መኪና ውስጥ መገኘቷን ፓሊስ አስታወቀ

ታትሟል

በፈረንሳይዋ መዲና ፓሪስ አካባቢውን የሚቆጣጠሩ ፖሊሶች በአንድ ቅንጡ መኪና ውስጥ የአንበሳ ደቦሏ እንደምትገኝ ጥሪ ደረሳቸው።

ፖሊሶች በአካባቢው ደርሰውም አረንጓዴ ላምቦርጊኒውን አስቁመው ሲመለከቱ ሾፌሩ ከአንበሳ ደቦሏ ጋር ፎቶ በመነሳት ላይ ነበር።

የ33 ዓመቱ ሾፌር "ድመት" መስላኝ ነው ብሎ ድርቅ ቢልም በቁጥጥር ስር ከመዋል አላደነውም።

ደቦሏ ፑቲን የሚል መጠሪያ ያላት ሲሆን የ ሁለት ተኩል ወራት ዕድሜ አላት።

መኪናው ውስጥ እንዴት ተገኘች ለሚለው ጥያቄ ፖሊሶች ሲመልሱ በአንድ መንግሥታዊ ካልሆነ ድርጅት ከሚደገፍ የእንስሳት መጠለያ ተወስዳ እንደሆነ ገልፀዋል።

ባለፈው ወርም እንዲሁ በተመሳሳይ ሁኔታ በፓሪስ የአንበሳ ደቦል በአንድ አፓርትመንት ውስት መገኘቱ ተገልጿል።