በመላው ዓለም 27.1 ሚሊዮን ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተገለፀ

እንደ ጆንስ ሆፕኪንስ መረጃ ከሆነ በመላው ዓለም 27.1 ሚሊዮን ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ሲረጋገጥ 889,000 ያህሉ ደግሞ ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ ህይወታቸውን አጥተዋል። አሜሪካ አሁንም ከዓለማችን አገራት ሁሉ በከፍተኛ ቁጥር በቫይረሱ የተጠቃች ስትሆን በዓለም ላይ ካለው የኮቪድ-19 ቁጥር አምስት እጁ በአሜሪካ ይገኛል ተብሏል። ሕንድ ብራዚል ይዛው የነበረውን ሁለተኝነት በመረከብ በቫይረሱ በከፍተኛ ከተጠቁ አገራት ቃሚ አገራት ተርታ በሁለተኛነት ተመድባለች። በሕንድ በቀን 75,000 ሰዎች በኮቪድ መያዛቸው ሪፖርት ይደረጋል። በኢትዮጵያም እስካሁን ድረስ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሰዎች ሲመረመሩ ከእነዚህም መካከል 58ሺህ 672 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

የቀጥታ ሽፋን

  1. በየደቂቃው በኮሮናቫይረስ የሚያዙና የሚሞቱ ሰዎች ቁጥርን የሚያሳይ ካርታ

  2. በኢትዮጵያ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ወደ 60 ሺ ተጠጋ

    ዕለታዊ መግለጫ

    በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 19 ሺህ 449 የላብራቶሪ ምርመራ 976 ሰዎች ኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

    በተመሳሳይ ባለፉት 24 ሰዓታት የ15 ሰዎች ሕይወት ያለፈ ሲሆን በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በቫይረሱ ምክንያት ሕይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 933 ደርሷል።

    482 ሰዎች ደግሞ ከኮሮናቫይረስ ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 21 ሺህ 789 መድረሱ ታውቋል።

    እስካሁን በኢትዮጵያ ለ1 ሚሊየን 63 ሺህ 454 ሰዎች ምርመራ የተደረገ ሲሆን በአጠቃላይ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 59 ሺህ 648 ሆኗል።

  3. የኡጋንዳ ገበሬዎች ከወረርሽኙ በኋላ እየከሰርን ነው አሉ

    ኡጋንዳ

    የፎቶው ባለመብት, Getty Images

    በኡጋንዳ ገበሬዎች በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ወቅት በቂ ምርት ቢሰበስቡም የትራንስፖርት መስተጓጎል እና የፍላጎት መቀነስ የገበያ ዋጋውን እንዳወረደባቸው ተገለፀ።

    ገበሬዎች ምርታቸውን በወደቀ ዋጋ ለመሸጥ መገደዳቸው ተገልጾ ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ ሱቆችና ሻጮች የሚገዙትን መጠን በመቀነሳቸው እንደሆነ ተገልጿል።

    የፍራፍሬና የአትክልት ዋጋ ከአምስት ወር በፊት ከነበረበት በግማሽ በመቀነሱ የተነሳ በገበያ ስፍራዎች ተጥለው መመልከት የተለመደ ሆኗል።

    ዶ/ር ጄምስ ካኒዬጂ፣ የኬኬ ፍሬሽ ፉድስ የበላይ ኃላፊ፣ ድርጅታቸው ወደ አውሮጳ ምግብ እንደሚልክ ገልፀው በዋጋ መጨመርና በትራንስፖርት አገልግሎት መስተገጎል የተነሳ መቸገራውን ተናግረዋል።

    ኃላፊው ወደ ባህር ማዶ በአውሮፕላን ምግቦችን ለመላክ ውድ መሆኑ እንደሚያሳስባቸው ተናግረዋል።

    “ወደውጪ የምንልከው የምግብ መጠን እንዲሁም የምግብ ዋጋ መቀነስ በአንጻሩ ደግሞ የበረራ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ መጨመር የውጪ ገበያውን ጎድቶታል” ብለዋል።

    በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ሰዎች ቤታቸው እንዲቀመጡ መታዘዙ የትራንስፖርት መስተጓጎል እንዲከሰት አድርጓል ሲሉም ተናግረዋል።

    የዓለም አቀፍ በረራዎች ሲጀመሩ የውጪ ገበያ ንግዱ ይስተካከላል ብለው እንደሚያምኑ የሚናገሩት ካንዬጂ በቅርቡ እንደቀድሞው ምርታውን ሸጠው መጠቀም እንደሚችሉ ተስፋ አድርገዋል።

  4. የሩሲያ መምህራን ክትባቱን በመቃወም ፊርማ አሰባሰቡ

    ክትባት

    የፎቶው ባለመብት, Reuters

    ከ1400 በላይ የሚሆኑ የሩሲያ መምህራን መንግስት አስተማሪዎች በአስገዳጅ ሁኔታ ይከተባሉ በሚል ያስተላለፈውን ውሳኔ በመቃወም በበይነ መረብ ፊርማቸውን ማሰባሰባቸው ተሰምቷል።

    የሩሲያ መንግስት መምህራንንና የጤና ባለሙያዎች በቅርቡ ፈቃድ የተሰጠውን ክትባት መጀመሪያ እንደሚወስዱት አስታውቆ ነበር።

    አስተማሪዎቹ ባስተላለፉት መልዕክት ክትባቱን መወሰድ እንደማይፈልጉ በመግለጽ መንግስት ለመከተብ ፈቃደኛ ያልሆኑ አስተማሪዎች ደሞዛቸው እንዲቀነስ አልያም ከስራቸው እንዲታገዱ ይደረጋል በሚል ማስፈራራቱ እንዳሳሰባቸው አስታውቀዋል።

    የአስተማሪዎቹ ማህበር ክሎም ስፑትኒክ ቪ የሚል ስያሜ የተሰጠው ክትባቱ ተገቢውን የሚከራ ጊዜ በአግባቡ ያልጨረሰ በመሆኑ ክትባቱን ከአሁኑ መጀመሩ አደጋ ሊኖረው ይችላል ብሏል።

    ባሳለፍነው አርብ ተመራማሪዎች ባወጡት ሪፖርት መሰረት ግን ክትባቱ የሰው ልጅን በሽታ የመከላከል አቅም እንደሚያነቃቃ አረጋግጠናል ብለዋል።

  5. ፖፕ ፍራንስ - ሐሜት ከኮሮናቫይረስ ይብሳል

    ፖፕ ፍራንሲስ

    የፎቶው ባለመብት, EPA

    ፖፕ ፍራንሲስ ትናንት በቫቲካን ለተሰባሰቡ ምዕመናን ሐሜት “ከኮቪድ ወረርሽኝ በላይ የከፋ ነው” ማለታቸው ተሰምቷል።

    ጳጳሱ በቫቲካን በነበራቸው ሳምንታዊ መልዕክእት ወቅት “እባካችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ፣ ላለማማት እንሞክር። ሰይጣን በሐሜት ጉልበቱ ፈርጣማ ነው። ሁልጊዜም ስለሌሎች መጥፎ ነገር ያወራል። ምክንያቱም ውሸታም በመሆኑና ቤተ ክርስትያንን ለመከፋፈል ስለሚሞክር ነው” ብለዋል።

  6. "ኮሮናቫይረስ ጠፋም አልጠፋ" በሚቀጥለው ዓመት ኦሊምፒክ ይካሄዳል

    ቶኪዮ ኦሎምፒክ

    የፎቶው ባለመብት, Getty Images

    በኮሮናቫይረስ ምክንያት ላልተወሰነ ጊዜ ተራዝሞ የነበረው የቶኪዮ ኦሊምፒክ በሚቀጥለው ዓመት በማንኛውም ሁኔታ እንደሚካሄድ ተገለጸ።

    የዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ምክትል ፕሬዝዳንት "ኮቪድ-19 ጠፋም አልጠፋ በሚቀጥለው ዓመት ኦሊምፒክ ይካሄዳል" ብለዋል።

    ጆን ኮትስ ለአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ እንዳረጋገጡት በሚቀጥለው ዓመት ኦሊምፒክ የሚጀምረው በሐምሌ 23 ይሆናል።

  7. በኢትዮጵያ የተደረገው የላብራቶሪ ምርመራ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሆነ

  8. ሕንድ በኮሮና በተያዙ ሰዎች ብዛት ብራዚልን በለጠች

    ሕንድ

    የፎቶው ባለመብት, Getty Images

    በሕንድ በኮሮናቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በፍጥነት እየጨመረ ይገኛል።

    ባለፉት 24 ሰዓታት እንኳ 90ሺህ ሰዎች በኮሮናቫይረስ መያዛቸው ስለመረጋገጡ የአገሪቱ የጤና ባለስልጣናት አስታውቀዋል።

    በዚህም ሕንድ ከብራዚል በልጣ አሜሪካን ተከትላ በዓለማችን በርካታ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች መገኛ ሁለተኛዋ አገር ሆናለች።

    አሁን በሕንድ 4 ሚሊዮን 204 ሺህ 613 ሰዎች በተህዋሲው ተይዘዋል። በተህዋሲው ተይዘው በሞቱ ዜጎች ቁጥርም ደግሞ ከዓለም 3ኛ ናት። እስካሁን 71ሺህ 642 ዜጎቿን አጥታለች።

    መንግሥት የሕንድን ኢኮኖሚ ካንቀላፋበት ለመቀስቀስ በሮቹን መከፋፈት መጀመሩን ተከትሎ ነው እንዲህ አይነት አስደንጋጭ ቁጥር መታየት የጀመረው።

    ባለፉት ሰባት ቀናት ያለማቋረጥ በቀን 75,000 ሺህ ሰዎች በአማካይ በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ ቆይቷል። ከዚህ በተጨማሪም በሕንድ ባለፉት ሰባት ቀናት በየቀኑ አንድ ሺህ ሰዎች በአማካይ ይሞቱባት እንደነበርም ተዘግቧል።

    ይህ ድንገቴ የቁጥር መጨመር የሕንድ የኮቪድ-19 የመመርመር አቅሟ ከማደጉ ጋር አብሮ የመጣ እንደሆነም እየተነገረ ነው።

    ሕንድ በቀን 1ሚሊዮንና ከዚያ በላይ ሰዎችን የመመርመር ደረጃ ላይ ደርሳለች።

  9. አውስትራሊያ 85 ሚሊዮን ክትባቶች ለዜጎቿ ልታቀርብ ነው

    አውስትራሊያ

    የፎቶው ባለመብት, Getty Images

    የአውስትራሊያው ጠቅላይ ሚንስትር አሁን እየበለጸጉ የሚገኙት ሁለቱ ክትባቶች ስኬታማ የሚሆኑ ከሆነ 85 ሚሊዮን ክትባቶችን መንግሥት ለሕዝቡ እንደሚያቀርብ አስታወቁ።

    ጠቅላይ ሚንስትር ስኮት ሞሪሰን አገራቸው የኮሮናቫይረስ ክትባት ለዜጎቿ በነጻ ለማቅረብ ሁለት የኮሮናቫይረስ ክትባቶችን ለመግዛት ስምምነቶችን ፈርማለች ብለዋል።

    እንደ ጠቅላይ ሚንስትሩ ከሆነ አውስትራሊያ ክትባቶቹን ለመግዛት 1.24 ቢሊዮን ዶላር ወጪ ታደርጋለች።

  10. ተጨማሪ 1206 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል

    BBC

    ትናንት በወጣው ዕለታዊ የኮሮናቫይረስ መግለጫ ላይ ለ25ሺህ 158 ሰዎች ምርመራ ተደርጎ 1206 ሰዎች ላይ ቫይረሱ መገኘቱ ተጠቁሟል።

    ይህም በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥርን ከ58ሺህ በላይ አድርሶታል።

    ከዚህ በተጨማሪም ትናንት በወጣው መግለጫ ላይ 531 ሰዎች ከበሽታው ማገገማቸው እና 21 ሰዎች ደግሞ ከኮቪድ-19 ጋር በተያያዘ ህይወታቸው ማለፉ ተጠቁሟል።