በኢትዮጵያ በአንድ ቀን 24 ሰዎች በኮቪድ-19 ሳቢያ ሞቱ
ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 23 ሺህ 712 የናሙና ምርመራ፤ 1303 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋገጠ።
የጤና ሚንስትር እና የሕብረተሰብ ጤና ተቋም ባወጡት ዕለታዊ መግለጫ እንደተመለከተው፤ በአንድ ቀን 24 ሰዎች ሕይወታቸው አልፏል።
ባጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 56 ሺህ 516 የደረሰ ሲሆን፤ 880 ሰዎች ደግሞ ሞተዋል።
ባለፉት 24 ሰዓታት 329 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል። ይህም በቫይረሱ ያገገሙ ሰዎችን ቁጥር 20 ሺህ 612 አድርሶታል።
እስካሁን 994 ሺህ 303 የናሙና ምርመራ ተደርጓል።