የምርጫ ጣቢያዎች ተዘጉ፤ ዲሞክራቶች በፍራቻ ላይ ሲሆኑ ሪፐብሊካን ደስታቸውን እየገለጹ ነው
በአሜሪካ የመጨረሻዎቹ የምርጫ ጣቢያዎች በአላስካ እና ሃዋይ ሲዘጉ እስካሁን ባሉ የቆጠራ ውጤቶች ዲሞክራቶች በፍራቻ ላይ ሲሆኑ ሪፐብሊካን ደስታቸውን እየገለጹ ነው።
እስካሁን ባሉ የቆጠራ ውጤቶችን መሰረት ባደረጉ ትንበያዎች መሰረት ዶናልድ ትራምፕ 246 ኢሌክቶራል ኮሌጅ ድምጾችን እንዳገኙ ሲገመት የዲሞክራቷ ካማላ ሃሪስ ደግሞ 194 ኢሌክቶራል ኮሌጅ እንዳገኙ ይታመናል።አንድእጩ ዋይትሃውስን ለማሸነፍ 270 ኢሌክቶራልኮሌጅ ማግኘትአለበት።
እስካሁን ድረስ በአሜሪካ ምርጫ ወሳኝ ከሚባሉት ውስጥ የሰሜን ካሮላይና እና ጆርጂያ ግዛቶችን ትራምፕ ማሸነፍ ችለዋል። እስካሁን ድረስ የአምስት ተጨማሪ ወሳኝ ግዛቶች ውጤት ባይታወቅም ቀደምት ትንበያዎች ትራምፕ በሁሉም እየመሩ እንደሆነ አሳይተዋል።.እነዚህስፍራዎች ካማላሃሪስ ወይምትራምፕ ሊያሸንፉባቸው የሚችሉ ተለዋዋጭነት ያላቸው ሲሆን የምርጫ ውጤቱንም የሚወስኑ እንደሆነ ተነግሯል።
የዲሞክራት ደጋፊዎች እና የምርጫው ስትራቴጂስቶች “ተስፋ የመቁረጥ ስሜት” እየተሰማቸው እንደሆነ ለቢቢሲው የምርጫ ዘጋቢ ተናግረዋል። በፍሎሪዳ የትራምፕ መቀመጫ ደግሞ ከፍተኛ ደስታ እየተገለጸ እንደሆነ ተዘግቧል።