ኢራን በባህሬን የሚገኝ የአሜሪካ አየር ኃይል ጦር ሰፈር ላይ ጉዳት ማድረሷን ገለፀች
ኢራን በባህሬን በሚገኝ የአሜሪካ አየር ኃይል ጦር ሰፈር ላይ የፈጸመችው የሮኬት ጥቃት ጉዳት ማድረሱን ገለፀች።
ፋርስ የተሰኘው የኢራን ዜና ወኪል ያጋራው ተንቀሳቃሽ ምስል ተከታታይ የሮኬት ጥቃቶች በርቀት የሚገኝ ዒላማ ላይ ሲወነጨፉ እና ሲፈነዱ ያሳያል።
የኢራን አብዮታዊ ዘብ በባህሬን ሼክ ኢሳ ክልል በሚገኝ የአሜሪካ አየር ኃይል ማዘዣ እና ሠራተኞች ሕንጻ ላይ የፈጸማቸው የድሮን እና የሚሳዔል ጥቃቶች የነዳጅ ታንኮች ማፈንዳቱን ገልጿል።
አሜሪካ በጉዳዩ ላይ እስካሁን የሰጠችው ምላሽ የለም።
ቀደም ሲል በባህሬን ከሚገኝ የአሜሪካ ጦር ሰፈር ጭስ ሲወጣ ታይቶ ነበር።
የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሜሪካውያን ከባህሬን እና ከሌሎች የመካከለኛው ምሥራቅ አገራት በፍጥነት ለቅቀው እንዲወጡ አስጠንቅቆ ነበር።