የዶናልድ ትራምፕ እና የካማላ ሐሪስ የመጨረሻዎቹ ቀናት ፍልሚያ

አሜሪካ በመጪው ማክሰኞ፣ ጥቅምት 26/2017 ዓ.ም በዓለም ዘንድ በጉጉት እየተጠበቀ ያለውን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫዋን ታካሂዳለች። ሪፐብሊካኑ የቀድሞው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና ዲሞክራቷ ምክትል ፕሬዚዳንት አገሪቷን በመጪው አራት ዓመታት ለመምራት እየተፋለሙ ይገኛሉ። አሜሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ ሴት ፕሬዝደንት ትመርጣለች ወይስ ዶናልድ ትራምፕ ለሁለተኛ ጊዜ መንበረ-ሥልጣኑን ይቆናጠጣሉ? ቢቢሲ አማርኛ የአሜሪካን ምርጫ የተመለከቱ ዘገባዎች በቀጥታ ያደርስላችኋል።

ጭምቅ ሃሳብ

  • ዶናልድ ትራምፕ 47ኛው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ሆነው ተመረጡ
  • የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ለትራምፕ ‘የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት’ አስተላለፉ
  • ትራምፕ “አስደናቂ ድል ተቀዳጀሁ” አሉ
  • ትራምፕ ፕሬዝዳንት ለመሆን ሲቃረቡ፣ ሪፐብሊካኖች በሁለቱም ምክር ቤቶች የበላይነት እየያዙ ነው
  • ሪፐብሊካኖች የህግ መወሰኛ ምክር ቤቱን ይቆጣጠራሉ- ትንበያ
  • የምርጫ ጣቢያዎች ተዘጉ፤ ዲሞክራቶች በፍራቻ ላይ ሲሆኑ ሪፐብሊካን ደስታቸውን እየገለጹ ነው
  • ትራምፕ ወሳኝ የምትባለውን የሰሜን ካሮላይና ግዛትን አሸነፉ
  • የአሜሪካዊ ፕሬዝደንታዊ ምርጫ ውጤት እንደ ሩሲያ እና ቻይና ላሉ ኃያላን ሀገራት ምን ይፈይዳል?
  • የፕሬዚዳንታዊ እጩዎቹ የምርጫ ዘመቻ በእምነት ላይ የተመሰረተ ነው?
  • የአይዋ ግዛት ለምን የትኩረት ማዕከል ሆነች?
  • “የጋዛን ጦርነት ለማስቆም የተቻለኝን ሁሉ አደርጋለሁ” ካማላ ሃሪስ
  • ከምርጫው ቀን በፊት ከ70 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ድምጽ ሰጥቷል
  • እስካሁን ባለው ሂደት ከ78 ሚሊዮን በላይ አሜሪካውያን ድምጻቸውን የሰጡ ሲሆን ይህም ከአራት ዓመት በፊት የነበረውን የመጀመሪያ መራጮች ተሳትፎ ክብረ ወሰን የሰበረ ነው