የአሜሪካ ጦር በኢራን ደሴት ላይ ‘ራስን የመከላከል’ ጥቃት መፈጸሙን እና ወደ መርከቦች
እና የባሕረ ሰላጤው አገራት የተተኮሱ ሚሳዔሎች እና ድሮኖችን መትቶ መጣሉን አስታወቀ።
የአሜሪካ ማዕከላዊ ዕዝ (ሴንትኮም) በሆርሙዝ ወሽመጥ እና ኣለይ በቄሸም ደሴት
ላይ “ኢራን ወደ መካከለኛው ምሥራቅ አገራት ልትፈጽም የነበረውን የጥቃት ሙከራ ተከትሎ” ጥቃት መሰንዘሩን አስታውቋል።
ኢራን ወደ ኩዌት ሁለት ሚሳዔሎችን ማስወንጨፏን ነገር ግን የታለመላቸውን ስፍራ ሳይደርሱ
መውደቃቸውን እንዲሁም ሦስት ወደ ባሕሬን የተወነጨፉ ደግሞ በአየር ላይ እንዲከሽፉ መደረጋቸውን ገልጿል።
የኢራን አብዮታዊ ዘብ በበኩሉ በቄሸም ደሴት በሚገኝ የግንኙነት ማማ ላይ ለተፈጸመ
ጥቃት በሰጠው ምላሽ በቀጣናው የሚገኙ የአሜሪካ የጦር ሰፈሮችን እና ሂሊኮፕተሮችን ማጥቃቱን በአገሪቱ መገናኛ ብዙኃን በኩል አስታውቋል።
ሴንትኮም በቄሸም ደሴት ላይ የተፈጸመው ጥቃት የኢራን ጦር የምድር መቆጣጠሪያ ጣቢያ፣
ኢራን “በቀጣናው ውሃዎች ላይ የማለፍ መብት ያላቸው ሰላማዊ ባሕረተኞች” ላይ የተኮሰቻቸውን ሦስት ድሮኖችን መትቶ መጣሉን አስታውቋል።
አብዮታዊ ዘቡ “የሆርሙዝ ወሽመጥን ደኅንነት ማወክ ጠብ አጫሪውን የአሜሪካ ጦር ከባድ ዋጋ ያስከፍለዋል” ሲል በመግለጫው ላይ አስታውቋል።
ኢራን በተደጋጋሚ የአሜሪካ ጦር ሰፈሮች በሚገኙባቸው ባሕሬን እና ኩዌት ላይ ጥቃቶቸን ፈጽማለች።
ቀደም ሲል ሴንቲኮም አሜሪካ የጣለችውን እገዳ ተከትሎ ወደ ኢራን እየቀዘፈ የነበረ ነዳጅ ጫኝ መርከብን ማጥቃቱን እና እንዳይንቀሳቀስ ማድረጉን አስታውቋል።
የአሜሪካ አየር ኃይል የቦትስዋናን ሰንደቅ ዓላማ የሰቀለ ነዳጅ ጫኝ መርከብ
በተደጋጋሚ የተሰጠውን ማስጠንቀቂያ ችላ ማለቱን ተከትሎ በሞተሩ ላይ ጥቃት መፈጸሙን ተገልጿል።
ሴንቲኮም ማክሰኞ ዕለት መርከቦ ላይ ጥቃት ሲፈጽም የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምሥል ያሠራጨ ሲሆን የኢራን ጦር በይፋ የሰጠው ምላሽ የለም።
ዕዙ በመግለጫው ከአውሮፓውያኑ ሚያዝያ 13 ጀምሮ አሜሪካ ወደ ኢራን ወደቦች የሚደረጉ
እንቅስቃሴዎችን ማገዷን አስታውሶ፣ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ 122 መርከቦች አቅጣጫቸውን አንዲቀይሩ እና እንዲመለሱ መደረጋቸውን አሻፈረኝ
ያሉትም ሞተራቸው እነዳይሠራ መደረጉን አስታውቋል።
ቢቢሲ የቦትስዋናን መንግሥት አስተያየት ለማግኘት ቢሞክርም አልተሳካም።
አሜሪካ ይህንን ጥቃት የፈጸመችው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ማርኮ ሩቢዮ በአገሪቱ ምክር ቤት ለመጀመሪያ
ጊዜ ቀርበው ስለ ኢራን ጦርነት ከተጠየቁ በኋላ ነው።