‘እያንዳንዱ ሰው ሁለት ወይም ሦስት የቤተሰቡ አባል በናዳ ተቀብሮበታል’
‘እያንዳንዱ ሰው ሁለት ወይም ሦስት የቤተሰቡ አባል በናዳ ተቀብሮበታል’
ታትሟል
እስካሁን ከ250 በላይ ሰዎች እንደሞቱበት በተረጋገጠው የጎፋ ዞን የመሬት መንሸራተት የተቀበሩ ሰዎችን ለማውጣት ፍለጋው አሁንም ቀጥሏል።
በአደጋው የሞቱ ሰዎች ቁጥር እስከ 500 ሊደርስ እንደሚችል የአካባቢው ባለሥልጣናት ይናገራሉ።
አካባቢው መሠረተ ልማት የሌለው እና ራቅ ያለ በመሆኑ የመቆፈሪያ መሳሪያዎችን ለማስገባት ባለመቻሉ ቁፋሮው በሰው እጅ እየተደረገ ነው።



